ሩሲያ፣ አሜሪካ የሩሲያን የደህንነት ጉዳይ በቁም ነገር የማትወስድ ከሆነ “ያለው ውጥረት ሊባባስ ይችላል” አለች
ሩሲያ ምዕራባውያን “የሞስኮን ቀይ መስመር እንዳያልፉ” ስታስጠነቅቅ ቆይታለች
በምስራቅ ዩክሬን ያለውን ግጭት ለመፍታት የተሄደው ርቀት ብዙም ተስፋ ሰጭ እንዳልሆነም ይገለጻል
አሜሪካ እና የኔቶ ጥምረት በፀጥታ ጋር በተያያዘ ከሩሲያ ጋር ለመነጋገር ፍላጎት ካላሳዩ የከፋ የፀጥታ ሁኔታ ሊገጥማቸው እንደሚችል የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ሪያብኮቭ አስገንዝበዋል፡፡
ሰርጌይ ሪያብኮቭ ይህንን ያሉት በዩክሬን ድንበሮች አከባቢ ያለውን ወታደራዊ ፍጥጫን በማስመልከት አሜሪካ እና ሩሲያ በጄኔቫ ብዙም አጥጋቢ ያልሆ ውይይት ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው፡፡
ሪያብኮቭ ሞስኮ የራስዋን ደህንነት ለማረጋገጥ የምእራቡ ዓለም ዋስትና የማትፈልግበት ደረጃ ላይ ለማድረስ ትሰራለች ማለታቸውንም ነው ሮይተረስ የሩሲያውን የዜና ወኪል /አር አይ ኤ/ ዋቢ በማድረግ ያወጣውን መረጃ ያመለክታል፡፡
ውይይቱ የ“ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት/NATO/ አለመቀላቀልን” በተመለከተ ያለውን ጥያቄ መመልከት ነበረበት የሚል ኃሳብም ሰንዝሯል የሩሲያው ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ሪያብኮቭ ።
ምዕራባውያን የሩሲያን ቀይ መስመር እንዳያልፉ ያስጠነቀቀችውን መልዕክት ከቁብ እየቆጠሩ እንዳልሆነ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከሳምነታት በፊት ማስታወቃቸው አይዘነጋም።
ቭላድሚር ፑቲን ምዕራባውያን የሞስኮን ቀይ መስመር እንዳያልፉ ብታስጠነቅቅም እነሰርሱ ግን በበቂ ሁኔታ በቁም ነገር እንዳልያዙት ገልጸዋል።
አሁን ላይ ሞስኮ ከምዕራባውያን ትክክለኛ የጸጥታ ኃላፊነት እንደምትፈልግ ተናግሯል፡፡
ፕሬዝዳንቱ በሞስኮ ለውጭ ፖሊሲ ባለስልጣናት በሰጡት ገለጻ በምስራቅ ዩክሬን ያለውን ግጭት ለመፍታት የተሄደው ርቀት ብዙም ተስፋ ሰጭ እንዳልሆነም መግለጻቸው ይታወሳል፡፡