ፌስቡክና ኢንስታግራም ከ2 ሺህ በላይ ሩሲያን የተመለከቱ ህገ ወጥ ናቸው የተባሉ ልጥፎችን ከገጻቸው አላነሱም
ሩሲያ የፌስቡክን በስሩ የሚያስተዳድረውን ሜታ ኩባንያ ላይ የ2 ቢሊየን የሩሲያ ሩብል ቅጣት አሳለፈች።
ሞስኮው የፌስቡክ ኩባንያው ሜታን የቀጣችው በህግ የተከለከለ ይዘት ያላቸውን ልጥፎች (ፖስትስ) ለማስወገድ ባለመቻሉ ነው።
ፌስቡክ እና ኢኒስታግራም ከ2 ሺህ በላይ ህገ ወጥ ናቸው የተባሉ ልጥፎችን ማንሳት ባለመቻላቸውን ሲ.ጂ.ቲ.ኤን ዘግቧል።
ይህንን ተከትሎም ፍርድ ቤቱ በፌስቡክ ሜታ ላይ የ2 ቢሊየን የሩሲያ ሩብል ወይም 27 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ቅጣት እንዲከፍል ወስኖበታል።
የሩሲያ ፍርድ ቤት ከዚህ ቀደምም ፌስቡክ፣ ጎግል እና ትዊተርን በአነስተኛ ገንዘብ መቅጣቱ የሚታወስ ሲሆን፤ የአሁኑ ቅጣት ግን ኩባንያዎቹ በሚያገኙት ገቢን መሰረት ያደረገ ነው ተብሏል።
ፌስቡክ ባለፍነው ሳምንት ውስጥ ሞስኮ ሕገወጥ ነው ብላ ያመነችውን ይዘት መሰረዝ ባለመቻሉ 17 ሚሊየን ሩብል ወይም 229 ሺህ 643 ዶላር ዕዳ መክፈሉን ይታወሳል።
በተያያዘ ዜና የሩሲያ ፍርድ ቤት በትናትናው እለት በግዙፉ የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጎግል ላይ የ7 ነጥብ 2 ቢሊዮን ሩብል (98 ሚሊዮን ዶላር) ቅጣት ማሳለፉ ይታወሳል።
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ግዙፍ የኢንተርኔት ኩባንያዎች የሃገሪቱን ህግ እየተላለፉ ነው ሲሉ ደጋግመው ከመውቀስም በላይ የሩሲያ ተጠቃሚዎቻቸውን መረጃ ማዕከላትን ገንብተው በዚያው በሃገራቸው እንዲያከማቹ ደጋግመው ተናግረዋል፡፡
ነገር ግን ይህ ጫናዎችን ለማድረግ በማሰብ ነው የሚሉ ትቶችን አስተናግዷል።