ፖለቲካ
ሩሲያ የሚሳይል አካል ለአሜሪካ ልኳል ያለችውን ግለሰብ በእስራት ቀጣች
በታስ ዜና አገልግሎት የተለቀቀው የሰርቢላንስ ቪዲዮ ካብኖቭ በሩሲያ ደህንነቶች ሲያዝ ይታያል
ሩሲያ የሚሳይል አካል ለአሜሪካ አስተላልፎ ሰጥቷል ያለችውን ግለሰብ በ12 1/2 ዓመት የሚቆይ እስራት ቀጣች
ሩሲያ የሚሳይሎ አካል ለአሜሪካ አስተላልፎ ሰጥቷል ያለችውን ግለሰብ በ12 1/2 ዓመት የሚቆይ እስራት ቀጣች።
የሩሲያ ፍርድ ቤት በላቲቪያ በኩል የሚሳይል አካል ለአሜሪካ ደህንነት በመስጠት ጥፈተኛ ነው ያለውን ግለሰብ 12 1/2 እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ ማሳለፉን ሮይተርስ ዘግቧል።
በከፍተኛ ጥንቃቄ በሚጠበቀው እስርቤት ጊዜውን እንዲያሳልፍ በትበር ፍ/ቤት የተወሰነበት ካብኖቭ የተባለው ግለሰብ በሩሲያ ኤየር ዲፌንስ ሚሳይል ሲስም እና በራዳር ቤዝድ ዊፐን ሲስተም ጥቅም ላይ የሚውል አካል አሽሽቶ አውጥቷል።
በታስ ዜና አገልግሎት የተለቀቀው የሰርቢላንስ ቪዲዮ ካብኖቭ በሩሲያ ደህንነቶች ሲያዝ ይታያል።
ከዚህ መተጨማሪ ታስ ካብኖቭ ፍርድቤት ቀርቦ ጥፋተኛ የተባለበትን የፍርድ ቤት ሂደት እና ፖሊስ ያቀረበበትን መረጃ አሳይቷል።
ሩሲያ በዩክሬን ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ መክፈቷን ተከትሎ አሜሪካን ጨምሮ ከምዕራባውያን ጋር የገባችበት ውጥረት እየከረረ መጥቷል።