ሰሜን ኮሪያ የአሜሪካ የጦር መርከብ ደቡብ ኮሪያ መድረሷን ተከትሎ ሚሳይል አስወነጨፈች
የጃፖን የመከላከያ ሚኒስቴር እንደገለጸው ሁለቱም ሚሳይሎች ከጃፖን የኢኮኖሚ ዞን ውጭ ማረፋቸውን ተናግሯል
የሚሳይሎቹን መተኮስ የሚያሳይ መረጃ እንዳላት የገለጸችው አሜሪካም ከአጋሮቿ ጋር እየመከረች መሆኑን ገልጻለች
ሰሜን ኮሪያ የአሜሪካ ባህር ሰርጓጅ የጦር መርከብ ደቡብ ኮሪያ ከደረሰች ከሰአታት በኋላ ሁለት የባለስቲክ ሚሳይሎችን አስወንጭፋለች።
የአሜሪካ ባለስቲክ ሚሳይል ተሸካሚ መርከብ ደቡቡ ኮሪያ ከደረሰች ከጥቂት ሰአታት በኋላ ሰሜን ኮሪያ ወደ ምስራቅ አቅጣጫ ሁለት ሚሳይሎች ማስወንጨፏን የጃፖን እና የደቡብ ኮሪያ ጦሮች አስታውቀዋል
የጃፖን የመከላከያ ሚኒስቴር እንደገለጸው ሁለቱም ሚሳይሎች ከጃፖን የኢኮኖሚ ዞን ውጭ ማረፋቸውን ተናግሯል።
የደቡብ ኮሪያ መከላከያ ስታፍ በበኩሉ ሰሜን ኮሪያ እንዲህ አይነት መኩራ እንድታቆም ጠይቋል።
ሰሜን ኮሪያ በተከታታይ የምታደርገው የባለስቲክ ሚሳይል ሙከራ የተመድን ጸጥታ ምክርቤት መርህ የሚጥስ እና በአጠቃላይ በኮሪያ ልሳነ ምድር አለመረጋጋት የሚያስከትል በመሆኑ በጽኑ እንደሚያወግዝ መከላከያ ስታፉ ገልጿል።
የሚሳይሎቹን መተኮስ የሚያሳይ መረጃ እንዳላት የገለጸችው አሜሪካም ከአጋሮቿ ጋር እየመከረች መሆኑን ገልጻለች።
ሰሜን በቀጣናው በምታደርገው የሚሳይል ማስወንጨፍ ተግባር ጃፖን በተደጋጋሚ ቅሬታ ታቀርባለች።
ነገርግን ሰሜን ኮሪያ፣ ደቡብ ኮሪያ አጋሮቿ ለሚያደርጉት ወታደራዊ ልምምድ ምላሽ ነው በሚል ሚሳይል ማስወንጨፏን ቀጥላለች።