ሩሲያ የከሰል ማዕድን ወደሚወጣባት የዩክሬኗ ሰሊዶቭ ከተማ በፍጥነት እየገሰገሰች መሆኗ ተነገረ
የሞስኮ ወታደሮች የዶምባስ ግዛትን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር እየሞከሩ ነው
የሰሊዶቭ መያዝ ሩሲያ ቁልፍ የሎጂስቲክ ማከፋፈያ ወደሆነችው የፖክሮቭስክ ከተማ ለምታደርገው እንቅሰቃሴ መንገድ የሚከፍት ነው ተብሏል
ሩሲያ የከሰል ማዕድን ወደሚወጣባት የዩክሬኗ ሰሊዶቭ ከተማ በፍጥነት እየገሰገሰች መሆኗ ተነገረ።
የሩሲያ ኃይሎች የከሰል ማዕድን ወደሚወጣባት የምስራቅ ዩክሬኗ ሰሊዶቭ ከተማ በፍጥነት እየገሰገሱ መሆናቸውን ሮይተርስ የሩሲያ መገናኛ ብዙኻንን እና የጦር ጸኃፊዎቸን ጠቅሶ ዘግቧል።
የሞስኮ ወታደሮች የዶምባስ ግዛትን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር እየሞከሩ ነው።
የሰሊዶቭ መያዝ ሩሲያ ቁልፍ የሎጂስቲክ ማከፋፈያ ወደሆነችውየፖክሮቭስክ ከተማ ለምታደርገው እንቅሰቃሴ መንገድ የሚከፍት ነው ተብሏል።
"የጠላት ምሽግ በድንገት ተደርምሷል" ሲል በዩክሬን የተወለደው እና የሩሲያ ደጋፊ የሆነው ታዋቂ የጦር ጸኃፊ ዩሪ ፖዶሊያካ ተናግሯል።
ሌሎች የሩሲያ ጦር ደጋፊ የሆኑ ጸኃፊዎችም ተመሳሳይ መረጃ ያጋሩ ሲሆን ሩሲያ ኃይሎች አሁን ላይ የተወሰነውን የሰሊዶቭ ክፍል ተቆጣጥረዋል ብለዋል።
ሞስኮቭስኪ ኮምሶሞሌት የተባለው የሩሲያ ጋዜጣ እንደዘገበው የሩሲያ ኃይሎች ከጦርነት በፊት 2ዐሺ ሰው ወደነበራት የሰሊዶቭ ከተማ መሀል እየተቃረቡ ናቸው።
የዩክሬን ጦር ዕዝ እንደገለጸው በሰሊዶቭ ከተማ አቅራቢያ በሚገኙ ግንባሮች ጠንካራ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን እና የሩሲያ የምድር ጥቃቷን ለማገዝ ተዋጊ እና ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖችን እየተጠቀመች ነው።
ዕዙ የሩሲያ ኃይሎች ወደ ከተማ ስለመግባታቸው ወይም የዩክሬን ኃይሎች ተሸንፈው ስለመልቀቃቸው ያለው ነገር የለም።
'ዲፕ ስትቴት' የተባለው የክሬንን የግንባር ሁኔታ የሚገመግም የካርታ ፕሮጀክት የሩሲያ ኃይሎች የሰሊዶቭን ምስራቃዊ ጫፍ መቆጣጠራቸውን እና አብዛኛው የከተማዋ መሀል ክፍል የግጭት ቀጣና መሆኑን ያሳያል።
እንደ ኦፕን ሶርስ ዳታ ከሆነ ምንም እንኳን ዩክሬን የሩሲያን ኩርስክ ግዛት ብትይዝም፣ ፑቲን በፈረንጆቹ 2022 "ለልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" ወደ ዩክሬን የላኳቸው ወታደሮች ከባለፈው መስከረም ወር ጀምሮ በፍጥነት ወደፊት እየገሰገሱ ይገኛሉ።
ሩሲያ በ2014 የያዘቻትን ክሬሚያን ጨምሮ 1/5 የሚሆነውን የዩክሬን ግዛት ይዛለች።