ሩሲያ የኑክሌር ኃይሏ ለውጊያ ያለውን ዝግጁነት ሞከረች
የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ፕሬዝደንት ፑቲን ሞስኮ ከአለም ግዙፍ የኑክሌር አቅም እንዳላት በተደጋጋሚ አስጠንቅቀዋል
ሩሲያ የያርስ ባለስቲክ ሚሳይል የታጠቀውን ከሞስኮ በስተሰሜን ምዕራብ የሚገኘውን የኑክሌር ኃይሏን የውጊያ ዝግጁነት መሞከሯ ተገልጿል
ሩሲያ በሰሜን ምዕራብ ያለው የኑክሌር ኃይሏ ለውጊያ ያለውን ዝግጁነት ሞክራለች።
ሩሲያ የያርስ ባለስቲክ ሚሳይል የታጠቀውን ከሞስኮ በስተሰሜን ምዕራብ የሚገኘውን የኑክሌር ኃይሏን የውጊያ ዝግጁነት መሞከሯን ሮይተርስ የሩሲያን መገናኛ ብዙኻን ጠቅሶ ዘግቧል።
በመሬት ወይም በሚኪና ላይ የሚጠመደው 11ሺ ኪሎሜትር የሚጓዘው ያርስ በርካታ የኑክሌር አረሮችን ማስወንጨፍ የሚችል ነው። ተንታኞች እንደሚሉት ሩሲያ ምዕራባውያን ከዚህ የበለጠ በዩክሬን ጦርነት እንዳይሳተፉ ለማድረግ በዚህ አመት በርካታ የኑክሌር ልምምዶችን አካሂዳለች።
ሩሲያ በቅርቡ ያደረገችው ልምምድ ኔቶ አመታዊ ልምምድ ባካሄደበት እና የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ "የድል" እቅዳቸውን ይፋ ባደረጉበት ተመሳሳይ ሳምንት ነው።
የሩሲያው ፕሬዝደንት ባለፈው ወር ሞስኮ የኑክሌር ጦር መሳሪያ ልትጠቀም የምትችልባቸውን ሁኔታዎች ዘርዝርዋል። ሩሲያ በአዲሱ የኑክሌር ፖሊሲዋ የኑክሌር ጦር መሳሪያ ልትጠቀምባቸው የምትችልባቸውን መስፈርቶች ከዚህ ቀደሙ ሰፋ አድርጋዋለች።
እንደዘገባው ከሆነ በትቨር ግዛት የሚገኘው የኑክሌር ኃይል በያርስ ሚሳይል 100 ኪሎሜትር የፈጀ ልምምድ ያደርጋል።
ሩሲያ ባለፈው ሐምሌ ወር በያርስ ሚሳይል ሁለት ጊዜ ልምምድ አድርጋለች። ከዚህ በተጨማሪም ሩሲያ ከባለስቲክ ሚሳይል ያነሰ ውጤታማነት እና ርቀት የሚሸፍኑ ታክቲካል የኑክሌር ጦር መሳሪያዎችን ለማዘጋጀት በዚህ አመት ሶስት ጊዜ ልምምድ አድርጋለች።
የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ፕሬዝደንት ፑቲን ሞስኮ ከአለም ግዙፍ የኑክሌር አቅም እንዳላት በተደጋጋሚ ቢያስጠነቅቁም፣ ወደ ኑክሌር ጦርነት መግባት አሰፈላጊ አለመሆኑን ይናገራሉ።