ወ/ሮ ሃና አርአያስላሴ የፍትህ ሚንስትር፤ ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ የቱርዝም ሚንስትር ተደርገው ተሹመዋል
ጌዲዮን ጥሞቲዮስ (ዶ/ር) የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ሚንስትር ሆነው ተሾሙ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በዛሬው እለት ለተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች አዳዲስ ሚኒስትሮችን ሾመዋል።
በዚህም መሰረት ጌዲዮን ጥሞቲዮስ (ዶ/ር)የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሆነው መሾማቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የፍትህ ሚኒስትር የነበሩት ዶ/ር ጌዲዮን ጥሞቲዮስ ባሳለፍነው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙትን አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴን በመተካት ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው የተሸሙት።
ወ/ሮ ሃና አርአያስላሴ የፍትህ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙ ሲሆን፤ የፍትህ ሚኒስትር የነበሩት ዶ/ር ጌዲዮን ጥሞቲዮስ ተከትለው ተሸመዋል።
ወ/ሮ ሃና አርዓያሥላሴ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡
ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ የቱርዝም ሚንስትር ተደርገው መሾማቸውንም ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ደኤታ በመሆን በማገልገል ላይ የነበሩት ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ፤ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ተክተው የቱሪዝም ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።