በእስራኤል የተገደለው የሐማስ መሪ ያህያ ሲንዋር ማን ነው?
የጥቅምት 7 ጥቃት ዋነኛ መሪ ሲንዋር እስራኤል ልትገድላቸው ከምትፈልጋቸው ሰዎች መካከል ቁጥር አንዱ ነበር
የ61 ዓመቱ ሲንዋር በጋዛ የእስራኤል ጦርን እየተዋጋ ነው የተገደለው ተብሏል
የእስራኤል ጦር አዲሱ የሐማስ መሪ ያህያ ሲንዋርን በትናትናው እለት በጋዛ ውስጥ በተደረገ ጦርነት መግደሉን አስታውቋል።
የሃማስ መሪ ያህያስ ሲንዋር በትናትናው እለት በደቡባዊ ጋዛ ውስጥ በተደረገ ኦፕሬሽን መገደላቸውን የእስራኤል ጦር አስታውቋል።
የ61 ዓመቱ የሃስ መሪ ያህያ ሲንዋር በጋዛ ውስጥ የእስራኤል ጦር ጋር እየተዋጋ መገደሉን የሚያሳዩ ምስሎችም ወጥተዋል።
ያህያ ስንዋር የቀድሞውን የሀማሱን ከፍተኛ መሪ ኢስማኤል ሀኒያን በኢራን ዋና ከተማ ቴህራን መገደልን ተከትሎ ነበር ሃማስን እንዲመሩ የተሰየሙት።
ሐማስ በእስራኤል ላይ የተፈጸመውን ያልተጠበቀ ጥቃት ከሀሳብ ማመንጨት ጀምሮ ጥቃቱን እንደመራ የሚታመነው ያህያ ሲንዋር፤ እስራኤል ልትገድላቸው ከምትፈልጋቸው ሰዎች መካከል ቁጥር አንዱ ነበር።
ያህያ ሲንዋር ማን ነው?
ያህያ ሲንዋር በፈረንጆቹ 1962 በደቡባዊ ጋዛ ክሃን ዩኒስ የሚገኝ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ውስጥ ነው የተወለደው።
ቤተሰቦቹ ማጃል አስከልን ከሚባለው እና በፈረንጆቹ 1968 ከእስራሌል እንደ ሀገርነት መቆርቆርን ተከትሎ አሸከለን ወደሚባል ስያሜ ከተለወጠ ስፍራ ነው የተፈናቀሉት።
በጋዛ እስላሚክ ዩንቨርስቲ የተማረው ያህያ ሲንዋር እድሜውን በትግል ያሳለፈ ሲሆን፤ በፈረንጆቹ 1988 የሃማስ የደህንነት ክፍልን አቋቁሟል
ሶስት የእስራኤል ወታደሮችን ገድሏል በሚል በ1989 በእስራኤል ታስሮ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት ሲንዋር ከ22 አመት እስር በኋላ በፈረንጆቹ 2011 በተደረገ የእስረኞች ልውውጥ ነበር የተለቀቀው።
በፈረንጆቹ 2017የሃማስ የጋዛ ሃላፊ ሆኖ ተመረጠው ሲንዋር፤ እስማኤል ሃኒየን ተከትሎ የሃማስ ዋነኛ መሪ ከመሆኑ አስቀድሞ የሃማስን ወታራዊ ክንፍም ሲመራ ቆይቷል።
ነሃሴ 2024 የኢስማኤል ሃኒየህ ግድያን ተከትሎ የሃማስ መሪ በመሆን የተመረጠ ሲሆን፤ ጋዛ ውስጥ ከእስራኤል ጦር ጋር በውጊያ ላይ እንዳለ መገደሉ ተነግሯል
ዝምተኛ ነው የሚባለው ሲንዋር የሐማስ ታጣቂዎች በጋዛ እስራኤልን ለመመከት ውጊያዎችን እየመራ እና እየተዋጋ እንደተገደለም ተገልጿል።
አሜሪክል በፈረንጆቹ 2015 ላይ ያህያ ሲንዋርን በዓለም አቀፍ ሽብርተኞች ዝርዝር ውስጥ በማካተት መያዝ ከምትፈልጋቸው ሰዎች ዝርዝር ውስጥ አካታው ነበር።