ሩሲያ እና አሜሪካ በሰሜን ኮሪያ ምክንያት በተመድ ስብሰባ ላይ ተጋጩ
በተመድ የሩሲያ አምባሳደር ቫስሊ ነበንዚያ እና በተመድ የአሜሪካ ምክትል አምባሳደር ሮበርት ውድ በሞስኮ በተጠራው የዩክሬን ጉዳይ ስብሰባ ላይ ሲካሰሱ ተደምጠዋል
የአሜሪካን ክስ ያስተባበሉት ሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያ ባለፈው አመት ወታደራዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር እንደሚሰሩ ቃል መግባታቸው ይታወሳል
ሩሲያ እና አሜሪካ በሰሜን ኮሪያ ምክንያት በተመድ ስብሰባ ላይ ተጋጩ።
አሜሪካ፣ ዘጠኝ ሰሜን ኮሪያ ሰራሽ ሚሳይሎችን ወደ ዩክሬን በማስወንጨፍ ሩሲያን ስትከስ ሩሲያ ደግሞ ባለፈው ወር የሩሲያ የትራስፖርት አውሮፕላን ተመቶ እንዲወድቅ ዋሽንግተን እጇ ተባባሪ ነበረች የሚል ክስ አቅርባለች።
በተመድ የሩሲያ አምባሳደር ቫስሊ ነበንዚያ እና በተመድ የአሜሪካ ምክትል አምባሳደር ሮበርት ውድ በሞስኮ በተጠራው የዩክሬን ጉዳይ ስብሰባ ላይ ሲካሰሱ ተደምጠዋል።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ የጀመረችው ከሁለት አመታት በፊት ነበር።
"እስካሁን ሩሲያ ሰሜን ኮሪያ ሰራሽ የሆኑ ሚሳይሎችን በትንሹ በዘጠኝ የዩክሬን ቦታዎች ላይ አስወንጭፋለች" ሲሉ ውድ 15 አባላት ላሉት የጸጥታው ምክርቤት ተናግረዋል።
ምክትል አምባሳደሩ በተመድ የጸጥታው ምክርቤት ውሳኔዎች አላከበሩም ያለቻቸው ሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያ ተጠያቂ መሆን አለባቸው ብለዋል።
የአሜሪካን ክስ ያስተባበሉት ሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያ ባለፈው አመት ወታደራዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር እንደሚሰሩ ቃል መግባታቸው ይታወሳል።
የዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ሩሲያ ከአሜሪካ ቅራኔ ውስጥ ካላቸው እንደ ኢራን እና ሰሜን ኮሪያ ካሉ ሀገራት ያላትን ግንኙነት እያጠናከረች መጥታለች።
ሩሲያ የጸጥታው ምክር ቤት እንዲሰበሰብ ያደረገችው ዩክሬን በምዕራባውያን የተሰጣት ሮኬት ተጠቅማ በፈጸመችው 28 ሰዎች ገድላለች ካለች በኋላ ነው።