ስድስት የበረራ አባላትና ሶሰት ወታደሮችን ጨምሮ 9 ሩሲያውያንም በአውሮፐላኑ ውስጥ ነበሩ
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በቤልግሮድ ተመትቶ ስለወደቀው የሩሲያ አውሮፕላን ዩክሬንን ተጠያቂ አደረጉ።
የዩክሬን ምርኮኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረው ኢዩሽን ll-76 የተሰኘው የወታደራዊ ትራስፖርት አውሮፕላን በዩክሬን ድንበር አቅራቢያ መከስከሱን ይታወሳል።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር እንደገለጸው አውሮፕላኑ በሩሲያ የጦር ምርኮኞች ሊቀየሩ የነበሩ 65 የዩክሬን የጦር ምርኮኖች አሳፍሮ ነበር።
አውሮፕላኑ 6 የበረራ ባለሙያዎችን፣ ስድስት ጠባቂዎችን ጨምሮ 74 ሰዎችን ይዞ ሲበር ነው አደጋው ያጋጠመው።
የውሮፕላኑን መከስከስ ተከትሎም ሩሲያ እና ዩክሬን እርስ በራሳቸውን ሲወነጃጀሉ ቆይተዋል።
የሩሲያው ፕሬዝዳት ቭላድሚር ፑቲን በአደጋው ዙሪያ ትናንት በሰጡት አስተያየት፤ በዩክሬን ድንበር አቅራቢያ የተከሰከሰውን አውሮፕላን መትታ የጣለችው ዩክሬን ነች ብለዋል።
የመጀመሪያ የምርመራ ውጤት በሁለት ወይም ሶስት ቀናት ውስጥ ይፋ ይሆናል ያሉት ፑቲን፤ ነገር ግን አውሮፕላኑን የመታው ሚሳዔል አሜሪካ ወይም ፈረንሳይ ሰራሽ ነው ብለዋል።
ፑቲን “ኢሊዩሺን ኢል-76 አውሮፕላን” 65 የዩክሬን የጦር እስረኞችን እንደጫነ ዩክሬን ታውቅ ነበር ሲሉም ዩክሬንን ከሰዋል።
“ዩክሬን ጥቃቱን ሆን ብላ ትፈጽም አሊያም በስህተት የማውቀው ነገር የለም” ያሉት ፑቲን፤ “ዩክሬን ጥቃቱን መሰንዘሯ ግን ግልጽ ነው” ብለዋል።