የአሜሪካ “ቢ-1” ቦምብ ጣይ አውሮፕላን እውነታዎች
በስአት 1 ሺህ 448 ኪሎሜትር የሚጓዘው “ቢ-1” በአንድ በረራ ማረፍ ሳይጠበቅበት መላው አለምን መዞር ይችላል
ጸረ መርከብ ሚሳኤልና ቦምቦችን ጨምሮ 216 ሺህ ኪሎግራም የሚመዝኑ እቃዎችን መሸከም እንደሚችልም ይነገራል
አሜሪካ በኢራቅና ሶሪያ የአየር ጥቃት “ቢ-1” በተሰኘ ቦምብ ጣይ አውሮፕላን ጥቃት ፈጽማለች።
ፔንታጎን በኢራን አብዮታዊ ዘብ እና በሚደግፋቸው ታጣቂዎች ላይ ከ85 በላይ ኢላማዎች ላይ ጥቃት የፈጸሙት ግዙፍ የሀገሪቱ የጦር አውሮፕላኖች መሆናቸውን ገልጿል።
ከባድ የጦር መሳሪያዎችን መሸከም የሚችለው ግዙፍ የአሜሪካ አየር ሃይል “ቢ1” ወይም “ቢ- 1ቢ” አውሮፕላን የኒዩክሌር ጥቃት ለመፈጸም ጭምር ጥቅም ላይ የሚውል ነው።
ይሁን እንጂ አሜሪካ ከሩሲያ ጋር የኒዩክሌር እሽቅድምድም ለማቆም ስትወስን ይህ አውሮፕላን ከፈረንጆቹ 2007 ወዲህ የኒዩክሌር መሳሪያዎችን እንዳይሸከም ተወስኗል።
ኢላማውን አይስትም የማይባለው "ቢ-1" ቦምብ ጣይ አውሮፕላን የአሜሪካ አየር ሀይል የሚተማመንበት የጦር አውሮፕላን ነው።
የቢ-1 ቦምብ ጣይ አውሮፕላን እውነታዎች
- ለመጀመሪያ ጊዜ አገልግሎት የጀመረው ጥቅምት 1984
- በኢራቅ ጦርነት በ1998 ድብደባ ፈፅሟል
- በአፍጋኒስታን፣ ሶሪያና ሊቢያም ቦምብ አዝንቧል
- ከውስጥም ከውጭም ከባድ መሳሪያዎችን ጭኖ በመጓዝ ጥቃት ያደርሳል
- ፀረመርከብ ሚሳኤሎችና ቦምቦችን ጨምሮ እስከ 216 ሺህ ኪሎግራም የሚመዝኑ መሳሪያዎችን መሸከም ይችላል
- አራት ሞተሮች ያሉት ሲሆን በስአት 1 ሺህ 448 ኪሎሜትሮችን ይጓዛል
- እየበረረ ነዳጅ መሙላትና በአንድ በረራ አለምን መዞር ይችላል
- 44.5 ሜትር ርዝመትና 10.4 ሜትር ቁመት አለው
- ከመሬት ወለል 9144 ኪሎሜትር ከፍ ብሎ መብረር ይችላለ
- 84 "ኤምኬ-82" የተሰኙ 500 ፓውንድ የሚመዝኑ ቦምቦችን መሸከም ይችላል
- 24 ከአየር ወደ ምድር የሚወነጨፉ ሚሳኤሎችን ተሸክሞ ያስወጭፋል
- የሚጓዝ ተሽከርካሪን ኢላማ ውስጥ በመክተት መምታት ይችላል