ፕሬዝደንት ፑቲን ሩሲያ ካጸደቀችው እና በአለምአቀፍ ደረጃ የኑክሌር ሙከራን ከሚያግደው ስምምነት የወጣችበትን ህግ ፈርመዋል
ሩሲያ 'ከአለምአቀፉ የኑክሌር ሙከራ እግድ ስምምነት' ወጣች።
ሩሲያ በአለምአቀፍ ደረጃ የኑክሌር ሙከራ እንዳይደረግ ከሚያግደው ስምምነት መውጣቷን አስታወቀች።
ፕሬዝደንት ፑቲን በትናንትናው እለት ሩሲያ ካጸደቀችው እና በአለምአቀፍ ደረጃ የኑክሌር ሙከራን ከሚያግደው ስምምነት የወጣችበትን ህግ መፈረማቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
የጦር መሳሪያ ህጎች እንዲከበሩ የሚጠይቁ ድርጅቶች የሩሲያን ከስምምነቱ የመውጣት ውሳኔ አውግዘዋል።
ይህ ወሳኔ ከ1962 የኩባ የኑክሌር ቀውስ ወዲህ በአሜሪካ እና በሩሲያ መካከል ዝቅተኛ ደረጃ ላይ የደረሰውን ግንኙነት የበለጠ ያቀዛቅዘዋል ተብሏል።
አሜሪካ በሩሲያ ውሳኔ በጣም እንደሚያሳስባት ገልጻለች።
"የሩሲያ ውሳኔ በአለምአቀፍ ደረጃ ያለውን የጦር መሳሪያ ቁጥጥር ወጣች።መን ችግር ውስጥ የሚያስገባ ነው" ሲሉ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ብሊንከን ተናግረዋል።
ሞስኮ ካጸደቀችው ኮምፕሪሄንሲቭ ኑክሌር ቴስት ባን(ሲቲቢቲ) የወጣችው ሩሲያን ስምምነቱን ፈርማ ካላጸደቀችው አሜሪካ ጎራ ለማሰለፍ ነው ብላለች።
አሜሪካ የማትጀምር ከሆነ ሩሲያ የኑክሌር ሙከራ እንደማታደርግ የሩሲያ ዲፕሎማት ተናግረዋል።
ነገርግን የወሰኑ የምዕራባውያን የጦር መሳሪያ ባለሙያዎች በዩክሬን ጦርነት እያካሄደች ያለችው ሩሲያ ለማስፈራራት የኑክሌር ጦር መሳሪያ ልትሞክር ትችላለች የሚል ስጋት አላቸው።
ፕሬዝደንት ፑቲን ግን ባለፈው ጥቅምት ወር ሩሲያ የኑክሌር ጦር መሳሪያ ሙከራ ትጀምራለች ወይስ አትጀምርም ለማለት ዝግጁ አለመሆናቸውን ገልጸው ነበር።