ፖለቲካ
አሜሪካ የኑክሌር መሳሪያ ወደ ፖላንድ የምትልክ ከሆነ የኑክሌር ጦርነት ይነሳል- ሜድቬዴቭ
ሩሲያ የታክቲካል የኑክሌር መሳሪያ ለመጀመሪያ ከግዛቷ ውጭ በቤላሩስ ማስቀመጧ አነጋጋሪ ሆኖ ነበር
ሜድቬዴቭ እንደተናገሩት አሜሪካ የፖላንድን ፍላጎት ለማሟላት የኑክሌር የጦር መሳሪያ በፖላንድ የምታስቀምጥ ከሆነ ጦርነት ይነሳል ብለዋል
አሜሪካ የኑክሌር የጦር መሳሪያ ወደ ፖላንድ የምትልክ ከሆነ የኑክሌር ጦርነት ሊነሳ ይችላል ሲሉ የቀድሞው የሩሲያ ፕሬዝደንት ዲሜትሪ ሜድቬዴቭ አስጠነቀቁ።
ሜድቬዴቭ እንደተናገሩት አሜሪካ የፖላንድን ፍላጎት ለማሟላት የኑክሌር የጦር መሳሪያ በፖላንድ የምታስቀምጥ ከሆነ ጦርነት ሊነሳ ይችላል ብለዋል።
በዚህ ሳምንት መጀመሪያ የፖላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞራዊኪ ኔቶ ፖላንድንም በኑክሌር ፕሮግራሙ እንዲያካትታት ጠይቀው ነበር።
ሜድቬዴቭ ለሩሲያው የዜና አገልግሎት ታስ እንደተናገሩት በፖላንድ ያሉት ባለስለጣናት ኃላፊነት የማይሰማቸው ናቸው ሲሉ ይከሳሉ።
ሜድቬዴቭ እነዚህ ሰዎች ስልጣን ላይ ካሉ የኑክሌር መሳሪያዎች ጥቅም ላይ ይውላሉ ማለት ነው ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።
ሩሲያ የታክቲካል የኑክሌር መሳሪያ ለመጀመሪያ ከግዛቷ ውጭ በቤላሩስ ማስቀመጧ አነጋጋሪ ሆኖ ነበር።
የሩሲያን እርምጃ አሜሪካን ጨምሮ ምዕራባውያን ሀገራት በጽኑ ተቃውመውት ነበር።