ሩሲያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ከዶላር ውጪ የንግድ ልውውጥ ክፍያዎችን ታደርጋለች- ፑቲን
ፑቲን ሞስኮ በንግድ ልውውጥ ክፍያዎች የየሀገራቱን ገንዘብ ለመጠቀም ዝግጁ ነች ብለዋል
በሩሲያ እና አፍሪካ መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ 18 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን የሩሲያው ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል
ሩሲያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር የንግድ ልውውጥ ክፍያዎችን በየሀገራቱ ገንዘብ ክፍያዎችን ለመፈጸም ዝግጁ መሆኗን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አስታወቁ።
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሩሲያ አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ሩሲያ በሩሲያ እና በአፍሪካ መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን አስታውቀዋል።
በሩሲያ እና በአፍሪካ መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ 18 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን የገለጹት ፐሬዝዳንቱ፤ በቅርብ ጊዜም ጉልህ በሆነ መጠን እድገት እንደሚያስመዘግብ ተናግረዋል።
- ሩሲያ ኤርትራን ጨምሮ ለአፍሪካ ሀገራት ለእያንዳንዳቸው ከ25 ሽህ እስከ 50 ሽህ ቶን እህል በነጻ እሰጣለሁ አለች
- ሩሲያ ስንዴዋን ለድሃ የአፍሪካ ሀገራት በነጻ ልትሰጥ እንደሆነ ተገለጸ
ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር ያላትን የንግድና የሰብአዊ ግንኙነቶች ይበልጥ ማሳደግ እንደምትፈልግም ነው ፕሬዝዳንት ፑቲን የተናገሩት።
ለዚህም ሞስኮ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር በገንዘብ ልማት ላይ ለመስራት እና የየሀገራን ገንዘቦች ለንግድ ክፍያዎች ለመጠቀም ዝግጁ መሆኗንም አስታውቀዋል።
በዚህ ረገድ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር የፋይናንሺያል መሠረተ ልማትን ለማጎልበት፣ የባንክ ተቋማትን በሩሲያ ከተፈጠረ የፋይናንሺያል መልእክት ማስተላለፊያ ሥርዓት ጋር ለማገናኘት ዝግጁ ነን ሲሉም ገልጸዋል።
ፑቲን በጉባዔው ላይ ባደረጉት ንግግር ሩሲያ ከአህጉሪቱ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት እና ንግድን ከስር መሰረቱ እንደሚያሳድግ እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።
ይህም የምዕራባውያን ገዳቢ ሥርዓቶች በመጣስ ድንበር ተሻጋሪ ክፍያዎችን እንዲፈጽም ያስችላል ሲሉም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።
በሴንትፒተርስበርግ ከተማ በመካሔድ ላይ በሚገኘው ጉባኤ ከ54 የአፍሪካ አገሮች የ49ኙ ተወካዮች እንደተገኙ ሩሲያ አስታውቃለች። ከእነዚህ መካከል 17 ርዕሳነ-ብሔር እና አራት የመንግሥታት መሪዎች ይገኙበታል።