ሩሲያ ኤርትራን ጨምሮ ለአፍሪካ ሀገራት ለእያንዳንዳቸው ከ25 ሽህ እስከ 50 ሽህ ቶን እህል በነጻ እሰጣለሁ አለች
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ፑቲን ለአፍሪካ ሀገራት እህል በነጻ እንደሚሰጡ ቃል ገቡ
ፑቲን የምዕራባዊያን ማዕቀብ ሞስኮ እህሏን እና ማዳበሪያዋን ወደ ውጭ ለመላክ አስቸጋሪ አድርጎታል ብለዋል
ሩሲያ ኤርትራን ጨምሮ ለሌሎች አፍሪካ ሀገራት ለእያንዳንዳቸው ከ25 ሽህ እስከ 50 ሽህ ቶን እህል በነጻ እንደምትሰጥ አስታወቀች።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለአፍሪካ መሪዎች በምዕራቡ ዓለም ማዕቀብ ቢጣልባቸውም በወራት ውስጥ 10 ሽዎች ቶን እህል እንደሚሰጡ ገልጸዋል።
ፑቲን የምዕራባዊያን ማዕቀብ ሞስኮ እህሏን እና ማዳበሪያዋን ወደ ውጭ ለመላክ አስቸጋሪ አድርጎታል ብለዋል።
በሴንት ፒተርስበርግ በተካሄደው የሩስያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ፕሬዝዳንቱ፤ ሩሲያ እጅግ ጥሩ የሆነ የእህል ምርት እየጠበቀች እንደሆነ ጠቅሰው፤ የዩክሬንን እህል ለመተካት የሞስኮ ሚና ነው ብለዋል።
- ፕሬዝዳንት ፑቲን ስንዴ የጫኑ መርከቦች ወደ ተቸገሩ ሀገራት ብቻ እንዲጓጓዙ እንደርጋለን አሉ
- ሩሲያ ስንዴዋን ለድሃ የአፍሪካ ሀገራት በነጻ ልትሰጥ እንደሆነ ተገለጸ
ለዚህም ዝግጁ ነን ያሉት ፑቲን፤ ለዓለም የምግብ ዋስትና ሲባል የሚደረግ እንደሆነ ተናግረዋል።
"በሚቀጥሉት ከ3 እስከ 4 ወራት ውስጥ ለቡርኪናፋሶ፣ ዚምባብዌ፣ ማሊ፣ ሶማሊያ፣ መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ እና ኤርትራ ለእያንዳንዳቸው ከ25 ሽህ እስከ 50 ሽሀሰ ቶን እህል ለማቅረብ ዝግጁ እንሆናለን" ሲሉ ፑቲን ተሳታፊዎች በጭብጨባ ተቀብለዋቸዋል።
"እነዚህን ምርቶች በነጻ ለተጠቃሚዎች እናቀርባለን" ሲሉም አክለዋል።
ጉባኤው እ.አ.አ. በ 2019 የተደረገው የሩሲያ-አፍሪካ የመጀመሪያ ስብሰባን ተከትሎ የመጣ ነው። አህጉሪቱ ላይ ተጽዕኖ ለመፍጠር እና የንግድ እንቅስቃሴን የማሳደግ አካልም ነው።
ሞስኮ የጥቁር ባህርን የእህል ስምምነት በማቋረጧ ከምዕራቡ ዓለም ለሚሰነዘርባት ትችት፤ ሩሲያ የራሷን እህልና ማዳበሪያ ለማሸጥ የነበራት ፍላጎት ወደ ጎን መባሉን ጠቅሰዋል።