በተቀጠረበት ዕለት 53 አይፎን ስልኮችን የሰረቀው ሰራተኛ
ግለሰቡ የሽያጭ ስራ አስኪያጅ ተደርጎ በተቀጠረበት ዕለት ብቻ ወደ ስርቆት ገብቷል ተብሏል
በፖሊስ የተያዘው ይህ ሰው 32 ሺህ ዶላር ዋጋ ያላቸው ስልኮችን መስረቁ ተገልጿል
በተቀጠረበት ዕለት 53 አይፎን ስልኮችን የሰረቀው ሰራተኛ
ስሙ ያልተጠቀሰው ይህ ግለሰብ በሩሲያዋ መዲና ሞስኮ ባለ አንድ የአይፎን ስልክ መሸጫ መደብር ውስጥ ነበር የተቀጠረው፡፡
ይህ ግለሰብ የሽያጭ ስራ አስኪያጅ ተደርጎ በተቀጠረበት መደብር ውስጥ ስራ በጀመረበት የመጀመሪያ ቀን 53 ስልኮችን መስረቁ ተገልጿል፡፡
ከሽያጭ መደብሩ ጥቆማ የደረሰው የሞስኮ ፖሊስ በድብቅ ካሜራ የተቀረጸ ተንቀሳቃሽ ምስል ያጋራ ሲሆን ግለሰቡም ወዲያውኑ ካለበት ሊያዝ ችሏል፡፡
ግለሰቡ ስልኮቹን ከመደብሮቹ ለምን እንደወሰደ ሲጠየቅም ስልኮቹን የወሰድኩት በሞስኮ ጎዳናዎች ላይ ለመሸጥ በማሰብ እንጂ ለመስረቅ አይደለም ሲል ምላሽ መስጠቱ ተገልጿል፡፡
ህንዳውያኑ ጥንዶች አይፎን ለመግዛት የ8 ወር ልጃቸውን ሽጠዋል
ከስልኮቹ በተጨማሪም በመሳቢያ ውስጥ የነበረ 570 ዶላር ወስዷል የተባለው ይህ ግለሰብ በፖሊስ ተጨማሪ ምርመራዎች እየተካሄዱበት ነውም ተብሏል፡፡
የ44 ዓመት ጎልማሳ የሆነው ይህ ግለሰብ ስራ ለመቀጠር ያስገባቸው የትምህርት ማስረጃዎች ሐሰተኛ እንደነበሩም ፖሊስ ሌንታ ለተሰኘው የሩሲያ ሚደያ ተናግሯል፡፡
በዚህ ሰራተኛ የተሰረቁት 53 አይፎን ሞባይሎች አጠቃላይ ዋጋቸው ሶት ሚሊዮን ሩብል ወይም 53 ሺህ ዶላር እንደሆኑም ተገልጿል፡፡