አፕል በአደጋ ወቅት ኔትዎርክ ከሌለበት ስፍራ በሳተላይት መልእት የሚልክ አይፎን 14 ይፋ አደረገ
አፕል ለስፖርተኞች የሚሆን “አልትራ” ስማርት ሰዓትም አስተዋውቋል
አፕል የመኪና አደጋ ቀደሞ መለየት የሚያችል ቴክኖሊጂ የተገጠመለት ስማርት ስልክም አስተዋውቋል
የአሜሪካው የቴክኖሎጂ ኩባያ አፕል በትናትናው ምሽት በበርካቶች ዘንድ ሲጠበቅ የነበረውን አይፎን 14 ስማርት ስልክን ጨምሮ ሌሎችም አዳዲስ የቴክኖለጂ ምርቶችን አስተዋውቋል።
አፕል ኩባያ በትናትናው እለት ባዘጋጀው መርሃ ግብር ላይ በቴክኖሎጂ የረቀቁ የአይፎን 14 ስማርት ስልኮች፣ ስማርት ሰዓት እንዲሁም የማዳመጫ ምርቶቹን ይፋ አድርጓል።
ክባያው ሁለት የአይፎን 14 ስማርክ ስልክ አይነቶችን ያስተዋወቀ ሲሆን፤ እነዚህም አይፎን 14 እና አይፎን 14 ፕላስ ናቸው።
ስማርት ስልኮቹ በቴክኖሎጂ የረቀቁ ናቸው የተባለ ሲሆን፤ ከዚህም ውስጥ በአደጋ ጊዜ ኔትዎርክ በሌለበት አካባቢ ላይ ስንሆን ከሳተላይት ጋር በመገናኘት መልእክት ለመላክ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ተገጥሞለታል።
ስማርት ስልኩ ያለ ሞባይል ኔዎርክ ከሳተላይት ጋር ተገናኝቶ መልእክት ለመላክ ዝቅተኛው 15 ሰከንድ ከፍ ካለ ደግሞ ጥቂት ደቂቃዎችን ሊፈጅበት ይችላል።
አዲሱ አይፎን 14 ከጀርባው ላይ ሶስት 12 ሜጋ ፒክስል ጥራት ያላቸው ካራዎች የተገጠሙ ሲሆን፤ የፊትለፊት (ሰልፊ) ካሜራውም 12 ሜጋ ፒከስል መሆኑ እና ለመጀመሪያ ጊዜ ራሱን የማስካከል ቴክኖሎጂም ተገጥሞለታል።
የአይፎን 14 ካሜራዎች ፈጣን እንቅስቃሴ ያላቸውን ቁሶች ፎቶ ማንሳት ጨምሮ በዝቅተኛ ብርሃን ፎቶ በማንሳት ረገድ 49 በመቶ ማሻሻያ እንደተረገም ኩባያው አስታውቋል።
ለስማርት ስልቹ የመሸጫ ዋጋ የተቆረጠላቸው ሲሆን፤ በዚህ የአይፎን 14 ዋጋ 799 የአሜሪካ ዶላር፣ የአይፎን 14 ፕላስ ደግሞ 999 ዶላር መሆኑም ታውቋል።
አፕል ኩባንያ ትናንት ካስተዋወቃቸው የቴክኖሎጂ ምርቶች ውስጥ ሲሪየስ 8 የተሰኘው ስማርት ሰዓትም ይገኝበታል።
ሲሪየስ 8 የተሰኘው ስማርት ሰዓት የመኪና አደጋ ቀደሞ መለየት የሚያስችል ቴክኖሊጂ የተገጠመለት ሲሆን፤ አደጋ ከደረሰ በኋላም የአደጋው የደረሰበትን አካባቢ የሚጠቁም መልእክት መላክ ይችላል ተብሏል።
ስማርት ሰዓቱ በተጨማሪም ለሴቶች የወር አበባን መከታተል እንዲሁም የሰውነትን ሙቀት በመለካት ክትትል ማድረግን ጨምሮ በርካታ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በውስጡ ይዟል።
አልትራ የተባለው ስማርት ሰዓትም አፕል ትናንት ካስተዋወቃቸው ውስጥ ሲሆን፤ በተለይም ለስፖርተኞች የሚያለግል ነው ተብሏል።
አልትራ ስማርት ሰዓት ውሃ የማያስገባ በመሆኑ ለዋነተኞች እንዲሁም በቀላሉ የማይሰበር እና አቧሯ የማያስገባ መሆኑ ደግሞ ለአትሌቶች እና ለሌሎችም ስፖርተኞች ያገለግላል።