ሩሲያ ከተኮሰ በኋላ አድራሻውን መቀያየር የሚችል ሚሳኤል ማዘጋጀቷን ገለጸች
ቶርናዶ የተሰኘው ይህ አዲስ ሚሳኤል በአንድ ጥቃት ብቻ ከ12 ስታዲየም በላይ ስፋት ላይ የተቀመጠን ጠላት ያወድማል ተብሏል
ጠላት በቀላሉ መለየት የማይችለው አዲሱ ሚሳኤል ወደ በዩክሬን ጥቅም ላይ እንደሚውል ተገልጿል
ሩሲያ ከተኮሰ በኋላ አድራሻውን መቀያየር የሚችል ሚሳኤል ማዘጋጀቷን ገለጸች።
የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ 15ኛ ወሩ ላይ ሲሆን ጦርነቱ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ቢባልም እሚቀጥል ይመስላል።
አሜሪካ እና ሌሎች የዓለማችን ሀገራት ለዩክሬን ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችን በመርዳት ላይ ናቸው።
ሩሲያ በበኩሏ ለዩክሬን የሚደረጉ የጦር መሳሪያ ድጋፎች ልዩነት እንደማይፈጥሩ ከዚህ በፊት አስታውቃለች።
ይህ በዚህ እንዳለ በየጊዜው አዳዲስ እና ከዚህ በፊት የተፈበረኩ የጦር መሳሪያዎችን በማዘመን ላይ ትገኛለች።
አሁን ደግሞ ቶርናዶ ኤስ የተሰኘ በየደቂቃው አድራሻውን መቀያየር የሚችል ሚሳኤል መስራቷን ገልጻለች።
እንደ አርቲ ዘገባ ይህ የጦር መሳሪያ አንድ ጊዜ በሚያደርሰው ጥቃት ብቻ ከ12 ስታዲየም በላይ ስፋት ላይ ያለን ስፍራ ማውደም ይችላል።
ባንድ ጊዜም 12 ሚሳኤል የሚተኩስ ሲሆን ወታደራዊ ማዘዣዎችን፣ የኮሙንኬሽን ማዕከላትን፣ የጦር መሳሪያ መካዝኖችን እና ሌሎች ወሳኝ የሚባሉ ወታደራዊ መሰረተ ልማቶችን እንደሚያወድም ተገልጿል።
ሚሳኤሉ ከተኮሰ በኋላ ወዲያውኑ አድራሻውን መቀየር መቻሉ የመልሶ ማጥቃት እንዳይከፈትበት ያደርጋልም ተብሏል።
እስከ 120 ኪሎ ሜትር ርቀት ድረስ ጥቃት መሰንዘር የሚያስችለው ይህ ሚሳኤል ለልዩ ዘመቻ በሚል ወደ ዩክሬን እንደሚላክ ተገልጻል።