ሰሜን ኮሪያ በጠላት ላይ "ከፍተኛ ቀውስ" ያስከትላል ያለችውን ሚሳይል መሞከሯን አስታወቀች
ሰሜን ኮሪያ አዲስ አህጉር አቋረጭ ሚሳይል ሙከራ ማድረጓን አስታወቀች
ደቡብ ኮሪያ እና አጋሮቿ በሚያካሂዱት ወታደራዊ ልምምድ የምትበሳጨው ሰሜን ኮሪያ በተደጋጋሚ የሚሳይል ሙከራዎችን በማድረግ ላይ ነች
ሰሜን ኮሪያ አዲስ አህጉር አቋረጭ ሚሳይል ሙከራ ማድረጓን አስታወቀች።
ሰሜን ኮሪያ የሀገሪቱን የኒውክሌር ጥቃት የመከላከል አቅምን ለማሳየት ህዋሶንግ-18 የተሰኘ አዲስ ባጥጥር ነዳጅ አህጉር አቀፍ ባሊስቲክ ሚሳኤል መሞከሯን የሀገሪቱ የመንግስት ሚዲያ ዘግቧል።
ሰሜን ኮሪያ አዲስ የውሃ ስር የኑክሌር ድሮን ሙከራ አደረገች
ሙከራውን የመሩት የሀገሪቱ መሪ ኪም ጆንግ ኡን ይህ ሚሳይል በጠላቶች ላይ ከፍተኛ ቀውስ የሚያስከትል ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ሰሜን ኮሪያ በቅርቡ የአሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ውጥረቱን እያባባሰ ነው ስትል ወቅሳ ከቅርብ ወራት ወዲህ የጦር መሳሪያ ሙከራዎችን አጠናክራለች።
ሰሜን ኮሪያ አሁንም መሳሪያውን እያመረተች መሆኑን እና ቴክኖሎጂውን ለመቆጣጠር ተጨማሪ ጊዜ እና ጥረት እንደሚያስፈልጋት ፒዮንግያንግ ተጨማሪ ሙከራዎችን ልታደርግ እንደምትችል ደቡብ ኮሪያ ገልጻለች።
የሰሜን ኮሪያ የመንግስት ሚዲያ ኬሲኤንኤ ኪም ከባለቤቱ፣ ከእህቱ እና ከሴት ልጃቸው ጋር በመሆን ሚሳይሉ ሲወነጨፎ ሲመለከት የሚያሳይ ፎቶግራፎች እና ሚሳይሉ በካሜራ መረብ የተሸፈነውን የሞባይል ላውንቸር ላይ አጋርቷል።
ሚሳይሉ የሰሜን ኮሪያን የመከላከል አቅም ይጨምራል ተብሏል።
ለሰሜን ኮሪያ ጥጥር ነዳጅ የሚጠቀም አህጉር አቋራጭ ሚሳይል መሞከር የረጅም ቁልፍ አላማ ነበር፤ ምክንያቱም በጦርነት ወቅት ሚሳይል በፍጥነት ለመላክ የሚያስችል መሆኑ ነው።
ደቡብ ኮሪያ እና አጋሮቿ በሚያካሂዱት ወታደራዊ ልምምድ የምትበሳጨው ሰሜን ኮሪያ በተደጋጋሚ የሚሳይል ሙከራዎችን በማድረግ ላይ ነች።