ፑቲን በሁለቱ ጦርነቶች እና በነዳጅ ጉዳይ ለመምከር መካከለኛው ምስራቅ ገቡ
ፑቲን ከኢምሬትሱ ሼህ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ነሃያን ጋር ለመምከር አቡዳቢ ገብተዋል
ፑቲን ከአቡዳቢ ወደ ሳኡዲ በማቅናት ከጥቅምት 2019 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከንጉስ መሀመድ ቢን ሳልማን ጋር በአካል ይገናኛሉ ተብሏል
ፑቲን በሁለቱ ጦርነቶች እና በነዳጅ ጉዳይ ለመምከር መካከለኛው ምስራቅ ገብዋል።
የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን በጦርነት እና በነዳጅ ጉዳይ መካከለኛው ምስራቅ ገብተዋል።
ፑቲን በዛሬው እለት ወደ ሳኡዲ አረቢያ በማቅናት ከንጉስ ሞሀመድ ቢን ሳልማን ጋር በነዳጅ ዘይት ምርት፣ በኦፐሰክ ፕላስ እና በጋዛ ሰርጥ እና በዩክሬን ባሉት ጦርነቶች ጉዳይ እንደሚመክሩ ሮይተርስ ዘግቧል።
ፑቲን ከንጉሱ ጋር የሚገናኙት የኦይል ወይም የነዳጅ ዘይት ዋጋ መቀነሱን ተከትሎ ነው።
በሩሲያ የሚመራው የነዳጅ ዘይት አምራች ሀገራት እና አጋሮች ጥምረት የሆነው ኦፔክ ፕላስ የዘይት ምርት ለመቀነስ ቢወስንም፣ የነዳጅ ዋጋ ቀንሷል።
ፑቲን ከኢምሬትሱ ሼህ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ነሃያን ጋር ለመምከር አቡዳቢ ገብተዋል።
ፑቲን ከአቡዳቢ ወደ ሳኡዲ በማቅናት ከጥቅምት 2019 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከንጉስ መሀመድ ቢን ሳልማን ጋር በአካል ይገናኛሉ ተብሏል።
ክሬሚሊን እንደገለጸው ፕሬዝደንት ፑቲን 40 በመቶ የሚሆነውን የአለም ነዳጅ በሚያቀርበው የኦፔክ ፕላስ ጉዳይ ይመክራሉ።
ክሬሚሊን "በአለምአቀፍ የነዳጅ ገበያ ውስጥ የተረጋጋ እና የሚተነበይ ሁኔታ እንዲኖር የሩሲያ እና ሳኡዲ የቅርብ ግንኙየት አስተማማኝ ዋስትና ነው" ብሏል።
የክሬሚሊን ኃላፊ በ2022 ወደ ኢራን በማቅናት ቀጣናውን ጎብኝተዋል።
ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ብዙም ወደ ውጭ የማይሄዱት ፑቲን ከማህመድ ቢን ሳልማን ጋር በእራኤል- ሀማስ ጦርነት፣ ሶሪያ እና የመን ሁኔታ እና በቀጣናው መረጋጋት በማስፈን ጉዳይ እንደሚወያዩ ክሬሚሊን ገልጿል።
በየቀኑ ወደ ገበያ ከሚረጨው 1/5 የሚሆነውን ነዳጅ የሚቆጣጠሩት ፑቲን እና መሀመድ ቢን ሳልማን አልፎ አልፎ በምእራባውያን ተግሳጽ ቢቀርብባቸውም፣ የቆየ መልካም ግንኙነት አላቸው።
የሀማስ እና እስራኤል ጦርነት አሜሪካ በቀጠናው የምትከተለው የፖሊሲ ውድቀት ነው የሚሉት ፑቲን ከኢራን እና ከአረብ ሀገራት ጋር ግንኙነታቸው እያጠናከሩ ነው።