ሩዋንዳ ለኢትዮጵያ ችግር ውስጣዊ መፍትሄ ከመመኘት ውጭ “ብዙም የምታደርገው የለም”፡ ፕሬዘዳንት ፖል ካጋሜ
ፕሬዝዳንቱ የሩዋነዳ ሚና “ኃሳብ ማወጣትና ማጋራት ነው” ሲሉም ነው የተናገሩት
ፕሬዘዳንቱ የችግሩ መጠን ከሰፋ ግን ጎረቤት ሀገራትና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የመፍትሄ አካል ለመሆን መሞከር የተለመደ ነው ብለዋል
ሩዋንዳ በኢትዮጵያ ያለውን ችግር ለመፍታት የሚያስችል ውስጣዊ መፍትሄ እንድታገኝ ከመመኘት ውጭ ብዙ የምታደርገው የተለየ ነገር እንደሌለ የሩዋነዳው ፕሬዝዳንት ፓል ካጋሜ ተናገሩ፡፡
የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ይህን ያሉት ከሩዋንዳ ብሮድካስቲንግ ኤጀንሲ ( አር.ቢ.ኤ) ጋር በነበራቸውና ሰፋ ያሉ ጉዳዮች በተነሱበት ቃለ-መጠይቅ ነው፡፡
ፕሬዝዳንቱ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታና የሩዋንዳ ሚናን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ በመንተራስ ምለሽ ሰጥተዋል፡፡
“ኢትዮጵያ የሩዋንዳ ወዳጅ ነበርች፣ናት እንዲሁም ሆና ትቀጥላለች” በማለት ንግግራቸው የጀመሩት ፖል ካጋሜ በቅርቡ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒሰትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በሩዋንዳ በነበራቸው ጉብኝት ሰፋ ያሉ ጉዳዮች አንስተው መወያየታቸው ገልጸዋል፡፡
- የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ኃላፊ በኢትዮጵያ ቆይታቸው የትግራይ እና አማራ ክልሎችን እንደሚጎበኙ ገለጹ
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሰራዊቱ ከትግራይ ክልል ስለመውጣቱ ምን አሉ?
ፖል ካጋሜ አሁን በኢትዮጵያ ሰሜን ክፍል፤ ትግራይ እና ትግራይ ክልል በሚያዋስኑ ክልሎችም ግጭት መኖሩን ተከትሎ ያጋጠመው ችግር ለማቃለል የተለያዩ አካላት ከመንግስት ጋር እየሰሩ መሆናቸው እንዲሁም የሰብዓዊ እርዳታ በማዳረስ በኩልም እየተሰራ መሆኑን እንደሚያውቁ አንስተዋል፡፡
“ሀገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ያስፈልጋታል፤ ይህ ጥያቄ ሌለው ጉዳይ ነው፡ ሀገሪቱ ያጋጠማትን ችግር ለመፍታት ምን እየሰራች ነው የሚለው ደግሞ ዋናው ነገር ነው”ም ነው ያሉት ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ፡፡
የችግሩ መጠን ከሰፋ ግን ወዳጅና ጎረቤት ሀገራት እንዲሁም የዓለም አቀፉ ማህበረስብ የመፍትሄ አካል ለመሆን መሞከር የተለመደ መሆኑን የገለጹት ፓል ካጋሜ፤ሩዋንዳ ተቃራኒ ኃይሎች ወደ ጠርጴዛ እንዲመጡ በማድረግ የመፍትሄው አካል ትሆናለችም ብለዋል፡፡
“ፕሬዝዳንቱ ሊኖረን የሚችለው ሚና “ኃሳብ ማወጣትና ማጋራት ነው” ሲሉም ነው የተናገሩት፡፡ ችግሩ የውስጥ ነው፤ ትግራይ የኢትዮጵያ አካል ናት፤ የሁለት ሀገራት ግጭት እንዳልሆነ መረዳት”እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡
የውስጥ ጉዳይ ነውና በሀገሪቱ በራሷ ነው መፈታት ያለበት የሚል እምነት እንዳለቸውንም ተናግሯል፡፡
“ሩዋንዳ ሁንም ቢሆን በኢትዮጵያ ያለውን ችግር እንዲፈታ ከመመኘት ውጭ የምታደርገው የተለየ ነገር የለም” ሲሉም ነው ፕሬዝዳንቱ ከሩዋንዳ ብሮድካስቲንግ ኤጀንሲ ( አር.ቢ.ኤ) ጋር በነበራቸው ቆይታ አስታውቀዋል፡፡