በትግራይ ክልል ግጭት የሚሳተፉ ሁሉም አካላት ተኩስ አቁመው ወደ ውይይት መምጣት አለባቸው- የፀጥታው ም/ቤት
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በትግራይ ክልል ግጭት ዙሪያ ውይይት አድርጓል
በሰብአዊነት ስም በኢትዮጵየ የውስጥ ጉዳይ ላይ የሚደረጉ ጣልቃ ገብነቶችን እንቃወማልን- ቻይና
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምር ቤት በትግራይ ክልል ግጭት ዙሪያ በዛሬው እለት ውይይት አድርጓል።
በውይይቱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ የተገኙ ሲሆን፤ በጦርነቱ የተካፈሉ አካላት በሙሉ የተኩስ አቁም እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
ምንም እንኳን የኢትዮጵያ መንግስት የተናጥል ተኩስ አቁም በማወጅ ከትግራይ ክልል ቢወጣም የህወሓት ሀይሎች ወደ ጎረቤት አፋር እና አማራ ክልሎች ጥቃት በመክፈታቸው አጠቃላይ የተኩስ አቁም ላይ መደረስ እንደልተቻለም ገልጸዋል።
ከወራት በፊት በትግራይ ክልል የተከሰተው ግጭት አሁን ላይ እየተስፋፋ መሆኑን እና በርካታ ሰብአዊ ኪሳራዎች እያስከተለ መሆኑን ተናግረዋል።
በጦርነቱ ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በየእለቱ እያሻቀበ መሆኑን እና ከ2 ሚሊየን በላይ ኢትዮጵያውያን ግጭቱን ተከትሎ መፈናቀላቸውን አስታውቀዋል።
ከትግራይ ክልል በተጨማሪም ወደ አማራ እና አፋር ክልል በተስፋፋው ግጭት ከ300 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውንም አስታውቀዋል።
ግጭቱ ከሰብአዊ ቀውስ በተጨማሪም የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ክፉኛ እየጎዳ ነው ያሉት ጉቴሬስ፤ የበሀገሪቱ የብድር ጣራ እየጨመ ነው፤ እዳ የመክፈል አቅሟ እየተዳከመ ጠወቷል፣ የኑሮ ውድነቱም በከፍተኛ ሁኔታ እያሸቀበ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ አንድነት እና የቀጠናው መረጋጋት ወሰሳኝ ናቸው ያሉት ጉቴርስ፤ አሁን ላለው ሁኔታ ወታደራዊ መፍትሄ የለም ሲሉም ተናረዋል።
በጦርነቱ የተካፈሉ አካት በሙሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የተኩስ አቁም እንዲያድርጉ፣ የውጭ ሀገራት ሀይሎች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ፣ ለሰብአዊ ድጋች መተላለፊያ መንገዶች እንዲከፈቱ እና ችግሩን ለመቅረፍ በኢትዮጵያ የሚመራ እና ሁሉንም አካታች የሆነ ውይይት እንዲካሄድ ጥሪ አቅርበዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ ውይይት እንዲጀመር ከአፍሪካ ህብረት እና ከሌሎች ሀገራ ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ዋና ጸሃፊው አስታውቀዋል።
የፈረንሳይ እና አየር ላንድ ተወካዮች በበኩላቸው በትግራይ ክልል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ የተፈጠሩ ነገሮች አሳሳቢ ናቸው ያሉ ሲሆን፤ የህወሓት ሀይሎች በአስቸኳይ ከወረሩት የአፋር እና የአማራ ክልል ለቀው እንዲወጡ፤ የአማራ ክልል ሀይሎች ከያዙት የትግራይ ክልል መሬት እንዲለቁ እንዲሁም ሁሉን አካታች የሆነ ውይይት እንዲጀመር ጥሪ አቅርበዋል።
የአሜሪካ ተወካይ በበኩላቸው፤ በአፋጣኝ ተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ ያልተገደበ የሰብአዊ ድጋፍ መስመር እንዲከፈት እና ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ያካተተ ውይይት እንዲጀመር አሜሪካ ጥሪ አቅርባ ነበረ፤እስካን የተጀመረ ነገር የለም፤ በኢትዮጵያ መንግስተ በኩልም በጎ ምለሽ አላገኘንም ብለዋል።
የህወሓት ሀይሎች ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች ገብተው በከፈቱት ጥቃት በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናላቸውን በመጥቀስ፤ ይህ በአፋጣኝ ሊቆም ይገባል ያሉ ሲሆን፤ “የኤርትራ ጦር በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ እየገባ ነው፤ አሁን ያለው የጦርነት እንቅስቃሴ እየተስፋፋ ነው፤ ይህም አሜሪካን ያሳስባታል” ብለዋል።
በሰሜን ኢትዮጵያ ባለው ሁኔታ ሚሊየኖች ለምግብ ችግር መጋለጣቸውን እና አሁን ባለው ሁኔታ በትግራይ ክልል ያሉ መጋዝኖች ውስጥ ክምችም ማለቁን በመጥቀስ፤ ለዚህም የኢትዮጵያን መንግስት ተወቃሽ አድርገዋል።
የህወሓት ሀይሎች የኤርትራ ስደተኞችን እያጠቁ ነው ያሉት ተወካዩ፤ “አንድ የሰብአው ድርጅት ሰራተኛም በህወሓት ሀይሎች ተገድሏል፤ በርካታ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ንብረቶችም በእነዚሁ ሀይሎች ተዘርፈዋል” ብለዋል።
“ወታደራዊ መፍትሄ የለም፤ በአፋጣኝ ወደ ተኩስ አቁም ይገባ” ያሉት ተወካዩ፤ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሁሉም ሀይሎች በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲመክሩ እና ሁሉን አካታች የሆነ ውይይት እንዲጀመርም ጠይቀዋል።
የሩሲያ ተወካይ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ መንግስት ባሳለፍነው ሰኔ ወር ላይ ያወጀው የተናጥል የተኩስ አቁም በህወሓት ሀይሎች መጣሱ አሳዛኝ መሆኑን ጠቅሰው፤ የህወሓት ሀይሎች ከትግራይ ክልል ውጪ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች ጥቃት መክፈታውን፤ የሀገር ውስጥ ፈናቃዮች ቁጥር በእጥፍ እንዲጨምር አድርጓል ብለዋል።
“የሰብአዊ ድጋፍ ጉዳይን ፖለቲካዊ ማድረግ ተገቢ አይደለም፣ በሚዲያ የሚካሄደው መርዛማ አካሄድ የመሳካጥትእድሉ አነስተኛ ነው” ያሉት የሩሲያ ተወካይ፤ ሰብአዊ ድጋች ሲቀርቡ ለትግራይ ብቻ ተብሎ ሳይሆን፤ ለአማራ፣ አፋር፣ ሶማሌ እና ኦሮሚያም ክልሎችም መሆን አለበት ሲሉም ተናግረዋል።
“በኢትዮጵየ ፖለቲካው ውይይት እንደጀመር እንደግፋለን፤ ነገር ግን ውይይቱ ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት በኢትዮጵያውያን መሪነት ሊካሄድ ይገባል”ም ብለዋል።
ለኢትዮጵያ የሚረጉ ድጋፎች የሀገሪቱን ሉአላዊነት እና አንድነት ባስጠበቀ መልኩ ሊካሄድ ይገባል ያሉ ሲሆን፤ በሰኔ ወር በተካሄደው ምርጫ ኢትዮጵያን የመረጡት መንግስት ሀገሪቱን ወደ ቀድሞ መስመር የመመለስ አቅም እንዳለውም የሩሲያ መንግስት ያምናል ሲሉም ተግረዋል።
የቻይና ተወካይም በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ ሁሉም አካላት በራሳቸውመ መንግድ በሚያድርጉት የፖለቲካ ውይይት ልዩነቶቻቸውን እንደሚፈቱ ቻይና ታምለች ብለዋል።
በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች ስራቸውን በሚሰሩበት ጊዜ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ባከበረ መልኩ መሆን ይገባል ያሉት ተወካዩ፤ ለኢትዮጵያ የሚደረገው የሰብአዊ ድጋፍም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
በሰብአዊ መብት እና በሰብዓዊ ድጋፍ ስም በኢትዮጵየ የውስጥ ጉዳይ ላይ የሚደረጉ ጣልቃ ገብነቶችን ቻይና አጥብቃ ትቃወማለችም ብለዋል።
የኬንያ እና የህንድ ተወካዮችም የትግራይ ክልል ግጭት መፍትሄ በኢትዮጵየውያን መሪነት መምጣት አለበት የሚል ሀሳብ አንስተዋል።
በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ መልእክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ፤ የህወሓትን ጸብ አጫሪነት ለምክር ቤቱ ያብራሩ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ መንግሰት ባሳለፍነው ሰኔ ወር ላይ ተኩስ አቁም አውጆ መውጣቱ በአካባቢው ለሰብአዊ እንቅቃሴ እንዲሁም ሰላም እና መረጋጋትን ለማምጣት ነበር ብለዋል።
ሆኖም ግን የህወሓት ሀይሎች ወደ ተኩስ አቁም የመምጣት ፍላጎት የላቸውም፤ ይባስ ብሎም ህጻናትን ወደ ውትድርና እያስገቡ ነው፤ ወላጆች ልጆቻውን ለውትድርና እንዲሰጡ እርዳታ እህልን እንደ ማስፈራሪያ እየተጠቀሙ ነው ብለዋል።
ህወሓት በአማራ እና በአፋር ክልሎች ላይ በከፈተው ጥቃት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀለቸውን እንዲሁም በህወሓት ተግባር ከትግራይ ክልል በተጨማሪ በአማራ እና አፋር ክልሎች የሚገኙ አርሶ አደሮች የግብርና ስራ መስራ እንዳልቻሉም አስረድተዋል።
ቡድኑ የእርዳታ እህሎች እንቅስቃሴን እያስተጓጎለ መሆኑን በመጥቀስ፤ ሀገሪቱ እንዳትረጋጋ ከተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀይሎች ጋር ጥምረት እየፈጠረ መሆኑን አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ ግብ ሰላም ነው፤ ነገር ግን ህወሓት በኢትዮጵያ እና በሰላም መካከል እንቅፋት ሆኖ ቆሟል ሲሉም ተናግረዋል።
ሁሉም አካል የህወሓት ቡድን ከዚህ ተግባሩ እንዲታቀብ ጫና እንዲፈጥሩ ጥሪ ያቀረቡት አማባሳደር ታዬ፤ ሁሉም የምክር ቤቱ አባላት እውነታ ላይ የተመሰረተ መረጃ ብቻ እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ኢትዮጵያ በልዩነት ውስጥ አንደነትን መፍጠር የቻለች ሀገር ነች፤ አሁን በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለው ለውጥም መድሎን ሳይሆን አንድነትን ማጠናከር ላይ የሚሰራ ነው ብለዋል።