የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ኃላፊ በኢትዮጵያ ቆይታቸው የትግራይ እና አማራ ክልሎችን እንደሚጎበኙ ገለጹ
ግሪፊትስ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከተለያዩ የሀገሪቱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገናኝተው የሚወያዩ ይሆናል
ኃላፊው ወደ ትግራይ ክልል በማቅናት በግጭቱ ምክንያት የተጎዱ ዜጎች ያነጋግራሉ ተብሏል
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) የሰብአዊ ጉዳዮች ኃላፊና የአስቸኳይ እርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊትስ በኢትየጵያ ወደ ትግራይና አማራ ክልሎች እንደሚሄዱ አስታውቀዋል፡፡
ኃላፊው ለ6ቀናት የሚቆይ የስራ ጉብኝት መጀመራቸውን ተመድ በመግለጫው አስታውቋል፡፡
ማርቲን ግሪፊትስ “ የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ኃላፊ እንደመሆኔ በኢትዮጵያ፤ የመጀመርያ ይፋዊ ጉብኝት ማድረጉ ትልቅ ፋይዳ አለው ብየ አምናለሁ” ብሏል፡፡
ኃላፊው “በትግራይ ክልል እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ባለው ግጭት፣ በአፋር፣ ሶማሌ እና ደቡብ ክልሎች ውስጥ ያሉ የጸጥታ ችግሮች እንዲሁም በሶማሌ፣በኦሮምያ እና በአፋር ክልል በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ኢትዮጵያ አሁን ላይ የሚያስፈልጋት የሰብዓዊ እርዳታ መጠን ጨምሯል”ም ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያን አሁን እያጋጠሟት የሚገኙ የጎርፍ መጥለቅለቅ፣ የአምበጣ ወረርሺኝ፣ ስር የሰደደ የምግብ ዋስትና እጥረት እና የኮቪድ ወረርሺኝ እንዳስደነገጣቸው የገለጹት ኃላፊው፤ ችግሩ በሚልዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸውም መሆኑንም ጠቁሟል፡፡
የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ኃላፊው ግሪፊትስ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከተለያዩ የሀገሪቱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንደሁም የተለያዩ የሰብዓዊ እርዳታ እና ለጋሽ ድርጅቶች ከወከሉ አካላት ጋር ተገናኝተው ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ኃላፊው ወደ ትግራይ ክልል በማቅናት በግጭቱ ምክንያት የተጎዱ ዜጎች እንደሚያነጋግሩ እና ከሰብዓዊ እርዳታ ስጭት ጋር በተያያዘ እየገጠሙ ያሉ ማነቆዎች የሚያጤኑም ይሆናል፡፡
በትግራይ ክልል 5.2 ሚልዮን (90 በመቶ) የሚሆን ህዝብ ሰብዓዊ እርዳታ እንደሚያስፈልገው ተመድ ሲገልጥጽ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ግሪፊትስ ወደ አማራ ክልል በማቅናት የክልሉ ባለስልጣናት ያናግራሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡፤
የሰብዓዊ እርዳታ ማህበረሰብ ከኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን የገለጹት፡፡አሁን ላይ 9 የተመድ ኤንሲዎች፣ ከአለም አቀፍ እና መንግስታታ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ እርዳታ ፍላጎት ለማሟላት እየሰሩ ይገኛሉ፡፡