የአካባቢ ወንጀሎችን ለመለየት ድሮኖች በአፍሪካ ጠቅም ላይ ሊጀምሩ ነው
የአከባቢ ወንጀሎች በዓለም ላይ ለሚኖሩ ሰዎች የዕለት ተዕለት ኑሮ እና ለመጪው ትውልድ ከባድ ስጋት ናቸው
የአካባቢ ወንጀሎችን ለመከላከል ድሮኖችን ለመጠቀም መወሰኗን ሩዋንዳ አስታውቃለች
የአካባቢ ወንጀሎችን ለመከላከል ሰው አልባ አውሮፕላኖችን (ድሮኖችን) ለመጠቀም መወሰኗን ሩዋንዳ አስታውቃለች።
የሀገሪቱ የምርመራ እና የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ድሮኖች የአካባቢ ወንጀሎችን ለመለየት ይሰማራሉ።
አንድ ሀገር የአካባቢ ወንጀሎችን ለመከላከል ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ሲትጠቀም ይህ በአፍሪካ አህጉር ውስጥ የመጀመሪያው ተሞክሮ ነው።
የአከባቢ ወንጀሎች በዓለም ላይ ለሚኖሩ ሰዎች የዕለት ተዕለት ኑሮ እና ለመጪው ትውልድ ከባድ ስጋት ናቸው።
ወንጀሎቹ ድንበርን የማይከተሉ እና ብዙውን ጊዜ እንደ ማጭበርበር፣ ሙስና፣ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና ግድያ ከመሰሉ ሌሎች ወንጀሎች ጋር አብረው ይፈጸማሉ።
የሩዋንዳ ውሳኔ በአፍሪካ አህጉር በአይነቱ የመጀመሪያው ነው።
የተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ጥበቃ ፕሮግራም እና ኢንተርፖል የአካባቢ ወንጀሎች ከአደንዛዥ እጽ፣ ሀሰተኛ እና ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር በኋላ በአራተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።
የሩዋንዳ የአካባቢ ጥበቃ ሚንስትር ዣን ዲ አርክ ሙግዋማሪያ ሰው ድሮኖች አካባቢን የሚጎዱ ተግባራትን ምላሽ ለመስጠት እና ለመቆጣጠር እንደሚረዳቸው አረጋግጠዋል።
ይህም የመሬት መራቆትን፣ የውሃ ብክለትን እና በተከለሉ ቦታዎች ላይ ህገ-ወጥ ደን መጨፍጨፍን ያካትታል ሲሉ የሀገር ውስጥ ጋዜጦች ዘግበዋል።
የተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ጥበቃ ፕሮግራም እና ኢንተርፖል እ.አ.አ. በ2016 ባወጡት ሪፖርት የአካባቢ ወንጀሎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል።
ወንጀሎቹ በደካማ ህጎች እና በአፈጻጸማቸው ምክንያት በ2015 የዓለም ኢኮኖሚ ላይ የ258 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ አስከትሏል።