46 በመቶ ኢትዮጵያዊያን የሳፋሪኮምን ቴሌኮም አገልግሎቶችን እንደተጠቀሙም ኩባንያው አስታውቋል
በኢትዮጵያ ሁለተኛው የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ ኩባንያ የሆነው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት አፈጻጸሙን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
እንደ መግለጫው ከሆነ የሳፋሪኮም ቴሌኮም አገልግሎቶች ለ46 በመቶ ኢትዮጵያዊያን የተዳረሰ ሲሆን የኔትወርክ ሳይቶች ብዛት ደግሞ ወደ ሶስት ሺህ ከፍ ብሏል፡፡
እንዲሁም የኩባንያው የዘወትር ደንበኞች ቁጥርም 6 ሚሊዮን መድረሱ ሲገለጽ የኤምፔሳ ድጅታል ግብይት መተግበሪያ ደንበኞች ደግሞ ከ8 ሚሊዮን በላይ እንደደረሰም ተገልጿል፡፡
በኤምፔሳ አማካኝነት የተፈጸመ ግብይት መጠን ከስድስት ቢሊዮን ብር በላይ እንደደረሰም ኩባንያው አስታውቋል፡፡