ኩባንያው በቀጣዮቹ ዓመታት 12 ሺህ የኔትወርክ ማሰራጫ ማማ እንደሚገነባም ገልጿል
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አገልግሎቱን በ280 ከተሞች ማዳረሱን አስታወቀ።
ከሁለት ዓመት በፊት በወጣ ዓለም አቀፍ ጨረታ ወደ ኢትዮጵያ የገባው ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት የተሰሩ ስራዎችን ሪፖርት ይፋ አድርጓል።
የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ዊም ቫንሄልፑተን በሰጡት መግለጫ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ደንበኞች 4 ነጥብ 1 ሚሊዮን ደንበኞች ማፍራቱን ተናግረዋል።
ኩባንያው የቴሌኮም አገልግሎቱን በ280 መካከለኛ እና አነስተኛ የኢትዮጵያ ከተሞች ማድረስንም ስራ አስፈጻሚው አስታውቀዋል።
በቀጣዮቹ ዓመታትም ከ10 ሺህ እስከ 12 ሺህ የኔትወርክ ማሰራጫ ማምዎችን የመገንባት እቅድ እንዳለውም ስራ አስፈጻሚው ጠቅሰዋል።
ባሳለፍነው ዓመት ከብሔራዊ ባንክ ፈቃድ የተሰጠው ኤምፔሳ የተሰኘው የድጅታል ፋይናንስ አገልግሎት ኤም-ፔሳ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ደንበኞች አፍርቷልም ተብሏል።