ሳውዲ አረቢያ በቀን 12 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ የማምረት አቅም ያላት ሀብታም ሀገር ነች
ሳውዲ አረቢያ አዲስ ድፍድፍ ነዳጅ ማግኘቷን ገለጸች፡፡
የዓለማችን ቀዳሚ ነዳጅ ላኪ ሀገር የሆነችው ሳውዲ አረቢያ ተጨማሪ የነዳጅ ሀብት ማግኘቷ ተገልጿል፡፡
የሀገሪቱ ዜና አገልግሎት እንዳስታወቀው በምስራቃዊ ሳውዲ አምስት አዲስ የነዳጅ ሀብት አግኝታለች፡፡
የሳውዲ መንግስታዊ የነዳጅ ኩባንያ የሆነው አርማኮ ሁለት የነዳጅ ማውጫ ስፍራዎችን እንዳገኘ የሀገሪቱ ኢነርጂ ሚኒስትር ልዑል አብዱላዚዝ ቢን ሳልማን ተናገረዋል፡፡
በምስራቃዊ ሳውዲ አረቢያ የተገኙት እነዚህ የነዳጅ ማውጫ አካባቢዎች በቀን በሚሊዮን የሚቆጠር በርሜል ነዳጅ ማምረት ያስችላሉ ተብሏል፡፡
አሁን ላይ ተገኙ የተባሉት የነዳጅ ሀብት ስፍራዎች ከዚህ በፊት ፍንጭ ተገኝቶባቸው ተጨማሪ ክትትል ሲደረግባቸው እንደቆየ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
ሳውዲ አረቢያ አሁን ላይ በቀን 12 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ በማምረት ላይ ስትሆን የዓለማችን ቁጥር አንድ ነዳጅ ላኪም ሀገር ናት፡፡
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከሳውዲ አረቢያ ይባረር ይሆን?
አሜሪካ ከ2018 ጀምሮ የዓለማችን ቀዳሚዋ ነዳጅ አምራች ሀገር ስትሆን በ2022 ላይ ብቻ በየቀኑ በአማካኝ 18 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ አምርታለች፡፡
ቬንዙዌላ፣ ሳውዲ አረቢያ፣ካናዳ፣ኢራን እና ኢራቅ በቅደም ተከተላቸው ዓለማችን አምስት ነዳጅ ሀብታም ሀገራት ሲሆኑ ሳውዲ አረቢያ በ2022 ዓመት ብቻ 311 ቢሊዮን ዶላር ከነዳጅ ሽያጭ ገቢ ማግኘቷ ተገልጿል፡፡
ኢትዮጵያ የነዳጅ ሀብት ካላቸው ዓለማችን ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን 428 ሺህ በርሜል ነዳጅ ሀብት በመያዝ 98ኛዋ ሀገር ተብላለች፡፡