አልናስር በአል ሂላል 2 ለ 0 ተሸንፎ የሳኡዲ ሊግን መምራት የሚችልበት እድል በመባከኑ የተበሳጩ ደጋፊዎች በተጫዋቹ ላይ ትችታቸውን ሰንዝረዋል
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከሳውዲ አረቢያ ሊባረር እንደሚችል ተገለጸ።
ፖርቹጋላዊው እና የሳውዲው አል ናስር እግር ኳስ ክለብ አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የሳውዲ አረቢያን ህግ መተላለፉ ነው የተነገረው።
አል ናስር እና አል ሂላል በሳኡዲ ፕሮኦ ሊግ ያደረጉት ጨዋታ በአልሂላል ሁለት ለዜሮ ድል መጠናቀቁ ይታወሳል።
ይህም አልናስር ሊጉን በ56 ነጥብ መምራት የሚያስችል እድል ይፈጥርለት ስለነበር ደጋፊዎች ክፉኛ ተበሳጭተዋል።
በዚህም ምክንያት የአልናስር ደጋፊዎች በክርስቲያኖ ሮናልዶ ላይ ተዋውሟቸውን ሲያሰሙ ታይቷል።
ደጋፊዎቹ ሮናልዶ ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ ወደ መልበሻ ክፍል በሚያመራበት ወቅት የአርጀንቲዊውን አጥቂ ሊዮኔል ሜሲን ስም ይጠራሉ።
በደጋፊዎቹ ድርጊት የተበሳጨው ክርስቲያኖ ሮናልዶም ብልቱን በመያዝ የአጸፋ ምላሽ ሰጥቷል ብለው ያምናሉ።
ደጋፊዎቹ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ "ደጋፊዎቹን የማያከብረው ተጫዋች ይባረር" በሚል ሃሽታግ ሮናልዶ ከአል ናስር እንዲሰናበት እየጠየቁ መሆኑ ተዘግቧል።
የሳውዲ አረቢያ ህግ ደግሞ በአደባባይ ያልተገቡ ነገሮች እንዳይደረጉ ይከለክላል።
ኑፍ ቢን አህመድ የተባለ የሳውዲ አረቢያ የህግ ባለሙያ ሮናልዶ የሀገሪቱን ህግ ጥሷል የሚል ክስ እንደሚመሰርት አስታውቋል።
ጠበቃው እንዳለው በሮናልዶ ላይ ክስ ከተመሰረተ በህጉ መሰረት ከሳውዲ አረቢያ ሊባረር እንደሚችል ነው የገለጸው።
ክለቡ አልናስር ግን "ሮናልዶ ጉዳት ደርሶበት ነው ሲወጣ የታየው ነገር የሆነው፤ ደጋፊዎች እንዳሻቸው ቢተረጉሙትም ተጫዋቹ ከገጠመው ጉዳት ጋር የተያያዘ መሆኑን መቶ በመቶ ማረጋጋጥ ይቻላል ማለቱን ሚረር ዘግቧል።