የቱሪዝም ቪዛ፣ ሸንገን ቪዛ፣ አሜሪካና እንግሊዝ ለመግባት ቪዛ ያገኙ ሁሉ የዑምራ ስርዓቶችን መፈጸም እንደሚችሉ ተነግሯል
የሳዑዲ ሀጅና ዑምራ ሚንስቴር በርካታ ሙስሊሞች ወደ ሀገሪቱ እንዲመጡ እና ኃይማኖታዊ ስርዓቱን እንዲፈጽሙ ለዑምራ ተጓዦች የኤሌክትሮኒክስ ቪዛ እየሰጠሁ ነው ብሏል።
ይህም ዑምራ ለማድረግ ህዝበ ሙስሊሙ የሚመጣበትን አሰራር ለማመቻቸት መንግስት የያዘው ማዕቀፍ ውስጥ ይገኛል ተብሏል።
የሳዑዲ የዜና ኤጀንሲ ለኤሌክትሮኒክስ ቪዛ ጥያቄዎች https://www.nusuk.sa/ar/about ማግኘት እንደሚቻል ገልጿል።
ከ1445 ሂጅራ የመጀመሪያ ወር ጀምሮ መጓዝ እንደሚቻል የተነገረ ሲሆን፤ ከሁሉም የዓለም ክፍሎች ወደ መካ እና መዲና የሚደረገው ጉዞ አሰራር ይሳለጣል ተብሏል።
እንዲሁም የመኖሪያ ቤት እና የመጓጓዣ አገልግሎቶችን ጨምሮ መረጃ እና ካርታዎች በበርካታ ቋንቋዎች ይቀርባሉ።
የሳዑዲ ሀጅ እና ዑምራ ሚንስቴር ከዚህ ቀደም ከትብብር ም/ቤት ሀገራት ለቱሪዝም ቪዛ ያገኙ፣ ሸንገን ሀገራት፣ አሜሪካ እና እንግሊዝ ለመግባት ቪዛ ያገኙ ሁሉ የዑምራ ስርዓቶችን መፈጸም እንደሚችሉ አስታውቋል።