ፈረንሳውያን ተጫዋቾችም ወደ ሳኡዲ ፊታቸውን እያዞሩ ነው
በፈረንጆቹ ነሃሴ 1 የጀመረው የሳኡዲ ፕሮ ሊግ የክረምት የዝውውር መስኮት ሊጠናቀቅ 20 ቀናት ቀርተዋል።
የሳኡዲ ክለቦች ከኔይማር እስከ ቤንዜማ፤ ከፊርሚኖ እስከ ሳዲዮ ማኔ በአውሮፓ ሊጎች የደመቁ ተጫዋቾችን ማስፈረማቸውን ቀጥለዋል።
ኔይማር ጁኒየር አል ሂላልን ሲቀላቀል በሳኡዲ ሊጎች የሚጫወቱ ብራዚላዊያንን ቁጥር 25 አድርሷል።
በዚህ የዝውውር መስኮት በርካታ የብራዚል፣ ፈረንሳይ እና ሴኔጋል ያላቸው ተጫዋቾች ወደ ሳኡዲ አቅንተዋል። ባለፈው አመት ጥር ወር አል ናስርን የተቀላቀለውን ክርስቲያኖ ሮናልዶ ፈረ የተከተሉ የሀገሩ ልጆችም ለሳኡዲ ክለቦች ፈርመዋል።