'ስቶክ ማርኬት' የግልና የመንግስት ድርጅቶች ገንዘብ ማግኛ አማራጮች እንዲያሰፉ የሚያስችል መሆኑ ተገለፀ
ድርጅቶች በኢትዮጵያው ስቶክ ማርኬት እንዴት እንደሚሳተፉ የሚተነተንበት የ'ስቶክ ማርኬት' ሴሚናር ተካሂዷል
ሴሚናሩ ድርጅቶች በኢትዮጵያው ስቶክ ማርኬት እንዴት እንደሚሳተፉ ማብራያ ተሰጥቶበታል
4ኛው የአይ ፒ ኦ 'ስቶክ ማርኬት' ሴሚናር በአዲስ አበባ ተካሄደ።
ስቶክ ማርኬት ማለት መደበኛ ባልሆነ መንገድ የተካሄዱ የአክሲዮን ሽያጮች (በየጊዜው ከፍ እና ዝቅ የሚሉ) መደበኛ የማድረግ ሂደት መሆኑ ይታወቃል።
የአክሲዮን ተሳታፊዎች መጠንም በከፍተኛ ደረጃ እንዲጨምር የሚያስችልም ነው።
በአዲስ አበባ ሸራተን ሆቴል በተካሄደው “አክሲዮኖችን ከኃብት ጋር ለማያያዝ ያለመ እንዲሁም ድርጅቶች በኢትዮጵያው ስቶክ ማርኬት እንዴት እንደሚሳተፉ የሚተነተንበት እንደሆነም ነው የተገለጸው።
በሴሚናሩ ” እንደ ሴሉላር ኮንሰልታንሲ፣ ግራንድ ቶርንተን አማካሪ፣ቢዲኦ እና ኮርነረ ስቶን አድቫይዘሪ ሰርቪስ የመሳሰሉ አማካሪ ድርጅቶች ተሳታፊ ሆነዋል።
በሴሚናሩ የተለያዩ ርእሶች ተነስተው ውይይት እየተደረገላቸውም መሆኑን የሴሉላር ኮንሰልታንሲ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር አቡሽ አያሌው ለዐል-አይን ኒውስ ገልጸዋል።
ዶ/ር አቡሽ ለዐል-አይን ኒውስ እንደተናገሩት የአይፒኦ/ኢኒሻል ፐብሊክ ኦፈሪንግ/ ተሞክሮ በሌሎች አገራት ምን ይመስላል..?፣ የሒሳብ ኦዲቲንግ እና የግመታ ስራ በአይኦፒ ጊዜ፣ እንዲሁም የኮርፖሬት አስተዳደር እና አይፒኦ በሴሚናሩ በከፍተኛ ባለሙያዎች የሚቀርቡ እና ውይይት የሚደረግባቸው አበይት አጀንዳዎች ናቸው ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በሴሚናሩ የተለያዩ አገራት በተለይም የአሜሪካ እና እንግሊዝ ስቶክ ማርኬት ላይ የነበሩ የአሰራር ተሞክሮዎች ምን እንደነበረና ልምዶቹ ለኢትዮጵያ እንዴት እንደሚጠቅሙ ውይይት ይደረጋልም ነው ያሉት ዶ/ር አቡሽ።
ገበያው ከሚያመጣቸው ልዩ ልዩ ጥቅሞች ውስጥ አንዱ የንግድ ድርጅቶችም ሆኑ የመንግስት ድርጅቶች ለሚያስፈልጋቸው የስራ ማስኬጃና የአቅም ግንባታ ማስፋፊያ አክስዮን ወይም ለቦንድ በመሸጥ ከማህበረሰቡ ገንዘብ የሚያገኙበት መንገድ መሆኑ ይታወቃል።
እናም ሴሚናሩ የግልም ሆኑ የመንግስት ድርጅቶች ገንዘብ ለማግኘት የሚያስችልዋቸው አማራጮች እንዲመለከቱ የሚያስችል እንደሆነ በመድረኩ ተገልጸዋል።
በሴሚናሩ የሚመለከታቸው የመንግስት ባለስልጣናት፣ የግሉ የንግድ ዘርፍ ስራ አስፈጻሚዎች፣ ኢንቨስተሮች እና ሚድያዎች ተሳትፈዋል።