ስፖርት
የሴኔጋል ፕሬዝዳንት የዛሬው ቀን የሕዝብ በዓል እንዲሆን ወሰኑ
በ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሴኔጋል ግብፅን በመለያ ምት 4ለ2 በማሸነፍ የአፍሪካ ዋናጫን ለመጀመሪያ ጊዜ አንስታለች
ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ሀገራቸው የአፍሪካ ዋንጫን ስታሸንፍ ጨዋታውን የተከታተሉት አዲስ አበባ ሆነው ነበር
ቡድናቸው የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ የሆነበትን ጨዋታ በአዲስ አበባ የተከታተሉት የሴኔጋል ፕሬዝዳንት የዛሬው ቀን የሕዝብ በዓል እንዲሆን ወሰኑ
በ35ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ የሕብረቱ የ 2022 ሊቀመንበርነትን የተረከቡት የሴኔጋል ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ብሔራዊ ቡድን የአህጉሩን ከፍተኛ የእግር ኳስ ሻምፒዮና በማሸነፉ የዛሬው ዕለት የሕዝብ በዓል እንዲሆን አወጁ።
የሴኔጋል ብሐየራዊ ቡድን የግብፅ አቻውን በመለያ ምት በማሸነፍ የአፍሪካ ዋንጫን በማሸነፉ የዛሬው ዕለት በመላው ሴኔጋል ሕዝባዊ በዓል ታውጇል።
በፈረንጆቹ በ2002 እና በ2019 ለፍጻሜ ደርሳ የነበረችው ሴኔጋል ውድድሩን ስታሸንፍ ይህ የመጀመሪያዋ ነው።
የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ሀገራቸው የአፍሪካ ዋንጫን ስታሸንፍ ጨዋታውን የተከታተሉት አዲስ አበባ ሆነው ነበር።
ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል የአፍሪካ ዋንጫን ያሸነፈውን ብሔራዊ ቡድን ነገ በቤተ መንግስታቸው እንደሚሸልሙት ቢቢሲ ዘግቧል።
በ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሴኔጋል ግብፅን በመለያ ምት 4ለ2 በማሸነፍ ነው የመጀመሪያ ዋንጫዋን ያሸነፈችው።