ካሜሩን የአፍሪካ ዋንጫ የተመልካቾችን ቁጥር ለመጨመር በሚል የስራና የትምህርት ሰዓቶችን ቀነሰች
የትምህርትና የስራ ሰአት ማስተካከያው እንደፈረንጆቹ ከጥር 7 እስከ የካቲት 4 ድረስ የሚቆይ ይሆናል
የትምህርትና የስራ ሰአት ማስተካከያው እንደፈረንጆቹ ከጥር 7 እስከ የካቲት 4 ድረስ የሚቆይ ይሆናል
ካሜሩን እያስተናገደች ያለውን የአፍሪካ ዋንጫ (AFCON) ወደ ስታዲየም ገብተው የሚመለከቱ ሰዎችን ቁጥር ለማሳደግ የስራ እና የትምህርት ሰዓት ላይ ቅነሳ ማድረጓን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አሰታወቁ።
ጉዳዩን በማስመለክት የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ዋና ፀሃፊ ሴራፊን ማግሎየር ፉዳ በሰጡት መግለጫ "የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎች በሚደረግባቸው ቀናት የትምህርት ቤቶች ሰዓት ከጠዋቱ 1:30 እስከ 7:00፤ የስራ ሰዓት ደግሞ ከጠዋቱ 1፡30 እስከ 8፡00 ይሆናል ብለዋል።
ይህ ልዩ የሰዓት ማሰተካከያ የተደረገው ካሜሩናውያን በዚህ ትልቅ አህጉራዊ ክስተት ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ለማስቻል ነው ብለዋል።
የትምህርት እና የስራ ሰዓት ማስተካከያው እንደፈረንጆቹ ከጥር 7 እስከ የካቲት 4 ድረስ እንደሚቆይም ተናግረዋል።
በስታዲየሞች በተለይም በዱዋላ፣ ባፉሳም እና ሊምቤ ከተሞች በተደረጉ የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎች ላይ ዝቅተኛ ተመልካቾች ያስተናገዱ እንደነበሩ የሚታወስ ነው።
የከተሞቹ ባለስልጣናት ለደጋፊዎች ወደ ስታዲየም የሚሄዱ እና የሚመለሱ የአውቶቡስ ማመላለሻዎችን በነጻ እንደሚሰጡ ተናግረዋል።
ደጋፊዎቸ ወደ ስታዲየም ከመግባታቸው በፊት እንዲከተቡ እና እንዲመረመሩ የሚያስገድዱ የፀረ-ኮቪድ-19 ክልከላ እርምጃዎች እና በሊምቤ ውስጥ የተገንጣይ ተዋጊዎች በአፍሪካ ዋንጫ ግጥሚያዎች ላይ የደቀኑት ስጋት ለተመልከች ቁፅር መቀነሽሷነኛ ምክንያት መሆናቸውን አንዳንድ የስፖርት ተንታኞች በመናገር ላይ ናቸው።
ባለፈው ሳምንት የጀመረውና በካሜሩን አስተናጋጅነት በመካሄድ ላይ ያለው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ በየካቲት 6 የሚጠናቀቅ ይሆናል።