የሴኔጋል የህገ መንግስት ምክር ቤት የተቃዋሚ ፓርቲ እጩ የሆኑት ባሲሮ ዲዮማየ ፈዬ ፕሬዝደይታዊ ምርጫውን ማሸነፋቸውን አረጋግጧል
የሴኔጋል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፈዬን አሸናፊነት አረጋገጠ ።
የሴኔጋል የህገ መንግስት ምክር ቤት የተቃዋሚ ፓርቲ እጩ የሆኑት ባሲሮ ዲዮማየ ፈዬ ፕሬዝደይታዊ ምርጫውን ማሸነፋቸውን አረጋግጧል።
ፈዩ የሀገሪቱ አምስተኛው ፕሬዝደንት ሆነው ቃለ መሀላ ይፈጽማሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ከፍተኛው ፍርድ ቤቱ በ100 የምርጫ ጣቢያዎች ላይ በተደረገው ቆጠራ መሰረት ባለፈው ረቡዕ እለት ይፋ የሆነውን ጊዜያዊ ውጤት አጽንቶታል።
ከተያዘለት ጊዜ ዘግይቶ በተካሄደው ፕሬዝደንታዊ ምርጫ የተቃዋሚ እጩ የሆኑት ፈዬ 54 በመቶ ድምጽ በማግኘት ነው ያሸነፉት።
በዚህ ምርጫ የገዥው ፓርቲ ጥምረትን በመወከል እጩ የነበሩት አማዶ ባ 35 በመቶ ድምጽ አግኝተዋል።
የስልጣን ዘመናቸው የተጠናቀቀውን ፕሬዝደንት ማኪ ሳልን የሚተኩት ፈዬ በመጭው ሚያዝያ ሁለት ቃለ መሃላ ይፈጽሟሉ ተብሏል።
ፕሬዝደንት ማኪ ሳል በፈረንጆቹ የካቲት 25 እንዲካሄድ ቀነ ገደብ ተቆርጦለት የነበረውን ምርጫ ማራዘማቻው በሀገሪቱ ከፍተኛ ተቃውሞ አስነስቶ ነበር።
የምርጫው መዘግየት በመፈንቅለ መንግስት በሚታመሰው ቀጣና ውስጥ ያለችውን ሴኔጋል መልካም ስም ያጎድፋል በማለት አለምአቀፍ አጋሮቿ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል።