የእስራኤል ፍርድ ቤት በአስገድዶ መድፈር የተከሰሱት የቀድሞ ዲፕሎማት ተላልፈው እንዲሰጡ ወሰነ
ሮይሜር ውሳኔው ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ቅሬታ ማቀረቢያ 30 ቀናት ተሰጥቷቸዋል ተብሏል
የእሰራኤል ፍርድ ቤት በሀገራቸው ፆታዊ ጥቃትና አስገድዶ መድፈር በመፈጸም የተከሰሱት የቀድሞ የሜክሲኮ ዲፕሎማት ተላልፈው እንዲሰጡ ውሳኔ አሳልፏል
የእስራኤል ፍርድ ቤት በአስገድዶ መድፈር የተከሰሱት የቀድሞ ዲፕሎማት ተላልፈው እንዲሰጡ ወሰነ።
የእሰራኤል ፍርድ ቤት በሀገራቸው ፆታዊ ጥቃትና አስገድዶ መድፈር በመፈጸም የተከሰሱት የቀድሞ የሜክሲኮ ዲፕሎማት ተላልፈው እንዲሰጡ ውሳኔ አሳልፏል።
- የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር በኦንላይን በተለቀቀው ሀሰተኛ የወሲብ ቪዲዮ ምክንያት ካሳ ጠየቁ
- የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻን እንደማትባርክ ገለጸች
በአሜሪካ የሜክሲኮ ሳንፍራንሲስኮ ቆንስላ ጀነራል እና የዩኔስኮ አምባሳደር የነበሩት አንድሬስ ሮይመር ሜክሲኮ ተላልፈው እንዲሰጧት በ2011 መጠየቋን ተከትሎ ባለፈው አመት በእሰራኤል በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ሮይመር ተላልፈው ከመሰጠታቸው በፊት የእስራእል የፍትህ ሚኒስትር መፈረም ይጠበቅባቸዋል። ፍትህ ሚኒስቴሩ ይህ መቼ ሊሆን አንደሚችል ያለው የለም።
የእየሩሳሊም ፍርድ ቤት ሮየመር ለጊዜው በቁም እስር እንዲቆዩ መወሰኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
ሜክሲኮ እና እሰራኤል ወንጀለኛን አስተላልፎ የመስጠት ስምምነት የላቸውም። የሜክሲኮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የእሰራኤል ፍርድ ቤት ውሳኔንን በበጎ ተቀብሎታል።
ሮይሜር ውሳኔው ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ቅሬታ ማቀረቢያ 30 ቀናት ተሰጥቷቸዋል ተብሏል።
እንደሜክሲኮ ጋዜጠኞቼ ማህበር ከሆነ ምንምእንኳን ክስ የመሰረቱት ጥቂቶች ቢሆኑም በሮሜር ላይ 60 የወሲባዊ ጥቃት ሪፖርቶች በ2021 ወጥተዋል።
በሮሜር ላይ ክስ ከመሰረቱት አንደኛዋ የሆነችው እዜል ስቻናስ ባለፈው ጥር ወር ለጋዜጠኞች እንደተናገረችው 184 ተመሳሳይ ማስረጃዎች ተሰብስበዋል።
ስቻናስ የእሰራኤል ፍርድ ቤት በቅርቡ ሮሜርን እንደሚልከው እና በሜክሲኮ ፍርድ ቤት ይቀረባል ብሏ ተስፋ እንደምታደርግ ተናግራለች።