ሩሲያ "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" ስትለው የነበረውን አሁን ለምን "ጦርነት" አለችው?
ጦርነት የሚለውን ቃል ላለመጠቀም ለረጅም ጊዜ ጥንቃቄ ሲያደርጉ የነበሩት ከፑቲን በተዋረድ ያሉት ባለስልጣናትም አሁን ላይ ጦርነት እያሉ መናገር ጀምረዋል
ሩሲያ ላለፉት ሁለት አመት በዩክሬን ያወጀችውን "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" አሁን ላይ ምዕራባውያን እየተሳተፉ ስለሆነ "ጦርነት" የሚል ስያሜ ሰጥታዋለች
ሩሲያ "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" ስትለው የነበረውን አሁን ለምን "ጦርነት" አለችው?
ሩሲያ ላለፉት ሁለት አመት በዩክሬን ያወጀችውን "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" አሁን ላይ ምዕራባውያን እየተሳተፉ ስለሆነ "ጦርነት" የሚል ስያሜ ሰጥታዋለች።
ሩሲያ በዩክሬን ያለውን ግጭት ጦርነት ነው በማለት ሩሲያውያንን ለረጅም እና ለከባድ ጦርነት ለማዘጋጀት አስባለችም ተብሏል።
የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮፕ ባለፈው አርብ እለት የሰጡት አስተያየት ለዩክሬን እና ለምዕራባውያን ጆሮ የሚስብ ላይሆን ይችላል። ነገርግን ሩሲያ ውስጥ ላለፉት ሁለት አመታት ጦርነቱን "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" እያሉ እንዲጠሩ ሲነገራቸው የነበሩት ሰዎች የግጭቱ ሁኔታ መቀየሩን እና ተጨማሪ መስዋትነት የሚጠበቅባቸው መሆኑን እንዲያውቁ ለማድረግ ነው።
"ጦርነት ውስጥ ነን። እውነት ነው፣ ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ በሚል ነበር የተጀመረው ነገርግን አሁን ምዕራባውያን በዩክሬን በኩል እየተሳተፉ ስለሆነ ጦርነት ሆኗል"ሲሉ ፔስኮብ 'አርጉመንት ኤንድ ፋክት' ለተባለው የሩሲያ መጽሄት ተናግረዋል።
ፔስኮብ አክለውም "በዚህ አምናለሁ። ሁለም ሰው ይህን አውቆ መንቀሳቀስ አለበት"ብለዋል።
ፔስኮብ ይህን ያሉት ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ለተጨማሪ ስድስት አመት በስልጣን የሚያቆያቸውን ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ካሸነፉ ከአምስት ቀናት በኋላ ነው።
ይህ ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት ጉዳይ ከአሜሪካ እና ከአጋሮቿ ጋር ለረጅም ጊዜ የተካረረ ፍጥጫ ውስጥ እንደምትቆይ የሚያመለክት ነው ተብሏል።
የፑቲን እና የፔስኮቭ ንግግር የሩሲያ ባለስልጣናት ለጦርነት ተጨማሪ ምልመላ እንዲያርጉ ፍቃድ የሚሰጥ ነው።
ፔስኮቭ እንዳሉት ሩሲያ በዩክሬን እያደረገችው ያለው ተግባር አሁንም ቢሆን በህግ "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" ተብሎ ነው የሚጠራው። ነገርግን ምዕራባውያን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እየተሳተፉ ስለሆነ ጦርነት ሆኗል ብለዋል ፔስኮቭ።
ጦርነት የሚለውን ቃል ላለመጠቀም ለረጅም ጊዜ ጥንቃቄ ሲያደርጉ የነበሩት ከፑቲን በተዋረድ ያሉት ባለስልጣናትም አሁን ላይ ጦርነት እያሉ መናገር ጀምረዋል።
ሩሲያ በከፊል የወረረቻቸውን አራት የምራቅ ዩክሬን ግዛቶች ሙሉ በሙሉ ለመጠቅለል ጦርነቱን እንደምትቀጥል ገልጻለች።