ስሙ በተመድ የሽብር መዝገብ ውስጥ ተካቶ የነበረው የአልቃ ኢዳ መሪ ተያዘ
አሜሪካ በፈረንጆቹ 2011 በሰሜን ፓኪስታን አቦታባድ ባደረሰችው የአየር ጥቃት ነበር ቢላደን ለረጅም ጊዜ ተደብቆበት በነበረበት ቦታ የተገደለው
ግለሰቡ በአሜሪካ ላይ የተፈጸመውን የ9/11 ጥቃት ካቀናበረው ከሟቹ ኦሳማ ቢን ላደን ጋር ግንኙነት አለው ተብሏል
ስሙ በተመድ የሽብር መዝገብ ውስጥ ተካቶ የነበረው የአልቃ ኢዳ መሪ ፓኪስታን ውስጥ ተይዟል።
የፓኪስታን የጸረ-ሽብር ባለስጣናት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) የሽብር መዝገብ ውስጥ የተካተተውን እና በአሜሪካ ላይ የተፈጸመውን የ9/11 ጥቃት ካቀናበረው ከሟቹ ኦሳማ ቢን ላደን ጋር ግንኙነት አለው የተባለውን አሚን ኡል ሀቅን በቁጥጥር ስር አውለዋል።
ፓኪስታን ከብዙ አመታት በኋላ የመጀመሪውን የአልቃ ኢዳ መሪ እስር የፈጸመችው፣ የሀገሪቱ የጸረ-ሽበር ክፍል(ሲቲዲ) ሀቅ ብዙ ህዝብ በሚኖርባት የፑንጃብ ግዛት ውስጥ በሚገኙ ወሳኝ መሰረተልማቶች ላይ ጥቃት ለማድረስ አቅዷል የሚል ክስ ካቀረበበት በኋላ ነው።
ሲቲዲ እቅዱ ምን እንደሆነ እና ተቋማቶቹ የትኞቹ እንደሆኑ አልገለጸም።
"ሲቲዲ ከደህንነት ተቋማት ጋር በመቀናጀት ባደረገው ስኬታማ የጸረ-ሽብር ዘመቻ ከፍተኛ የአልቃ ኢዳ መሪ የሆነውን አሚን ኡል ሀቅን በቁጥጥር ስር አውሏል" ብሏል የሲቲዲ ቃል አቀባይ ባወጣው መግለጫ።
"ስሙ በተመድ የሽብር ዝርዝር ውስጥ ተካቷል" ሲል ቃል አቀባየሐ አክሎ ገልጿል።
የተመድ "ሳንክሽን ፓኔል ኦን አይኤስአይኤለ' በፈረንጆቹ 2001 ባሰፈረው መዝገቡ ላይ አሚን ሙሀመድ ኡል ሀቅ ሳም ካን የተባለው ይህ ግለሰሰብ የቢን ላደን የጸጥታ ጉዳይ አስተባባሪ ነበር ብሏል። ፓኔሉ ሀቅ ከቢላደን ወይም ከታሊባን ጋር ግንኙነት ያለው እና የጦር መሳሪያ "በማቅረብ፣ በመሸጥ እና በማዘዋወር" እና በመሳሰሉት ተግባራት መሳተፉን ይገልጻል።
አሜሪካ በፈረንጆቹ 2011 በሰሜን ፓኪስታን አቦታባድ ባደረሰችው የአየር ጥቃት ነበር ቢላደን ለረጅም ጊዜ ተደብቆበት በነበረበት ቦታ የተገደለው።