የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የአልቃኢዳ መሪ አይማን አል ዘዋሪ መገደሉን አስታወቁ
ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ኦሳማ ቢላደንን ተክቶ የነበረውን የአልቃኢዳ መሪ አይማን አል ዘዋሂሪ መገደሉን አስታውቀዋል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የአልቃኢዳ መሪ አይማን አል ዘዋሂሪ መገደሉን አስታወቁ።
የሽብር ቡድኑ መሪ፤ የአሜሪካ የስለላ ተቋም (ሲአይ ኤ) በፈጸመው የድሮን ተልዕኮ መገደሉን ጆ ባይደን አረጋግጠዋል። የቀድሞውን መሪ ኦሳማ ቢላደንን በመተካት አል ቃኢዳን ሲመራ የነበረው ትውልደ ግብፃዊው የተገደለው በአፍጋኒስታን ካቡል መሆኑንም ጆ ባይደን ተናግረዋል።
አይማን አል ዘዋሂ ሪየተገደለው የሽብር ቡድኑን ቁልፍ መሪዎችን ኢላማ በማድረግ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት እንደሆነም ተገልጿል።
የአል ቃይዳ መሪ አፍጋኒስታን ውስጥ መገደሉን ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በሰበር ዜናነት እየዘገቡት ነው።
በጥቃቱ ዙሪያ መግለጫ የሰጡት የአሜሪካው ኘሬዝደንት ጆ ባይደን ፤ እርምጃ የተወሰደበት አይማን አል ዘዋሂሪ በኒውዮርክ ከተማ በመንትያ ህንጻዎች የተፈጸመውን ጥቃት ካቀነባበሩት መካከል አንዱ እንደሆነም ተናግረዋል።
የሽብር ቡድኑ መሪ መገደል የመስከረሙ ጥቃት መዝገብ መዘጋቱን የሚጠቁም መሆኑንም ገልጸዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት፤ አል ቃይዳ መሪ መገደሉ፤ የቱንም ያህል ጊዜ ቢወስድም በመስከረም 11 ጥቃት የተጎዱት ዜጎች ፍትህ ማግኘታቸውን ያመለክታል ብለዋል።
ባይደን፤ የቡድኑ መሪ አይማን አል ዘዋሂሪ እንዲደመሰስ ላደረጉ የሀገራቸው የጸጥታ ኃይሎች ምስጋና አቅርበዋል። ባይደን በካቡል በተደረገው ጥቃት ንጹኃን ኢላማ እንዳልተደረጉ ቢገልጹም ታሊባን ግን አጣጥሎታል።
በአፍጋኒስታን የተደረገውንና የአል ቃይዳ መሪ የተገደለበትን ጥቃት ታሊባን አውግዞታል። የወቅቱ የአፍጋኒስታን ገዥ ታሊባን፤ አሜሪካ ጥቃት ያደረሰችው በመኖሪያ ቤት አካባቢ ነው ብሏል።
የአል ቃይዳ መሪ አይማን አል ዘዋሂሪ
ከአንድ ዓመት በፊት እንደሞቱ ሲነገር ቢቆይም የመስከረም 11ዱ ጥቃት 20ኛ ዓመቱ ሲታሰብ አዲስ ተንቀሳቃ ቪዲዮ ለቀው እንደነበር ይታወሳል።