ፖለቲካ
ከፍተኛ የሂዝቦላ ኮማንደር በእስራኤል የአየር ጥቃት መገደሉ ገለጸ
ሀማስ በደቡብ እስራኤል ጥቃት ከሰነዘረበት ከባለፈው አመት ጥቅምት ወዲህ በእስራኤል የአየር ድብደባ 130 የሂዝቦላ አባላት ተገድለዋል
አል ታዊል እና ሌላ የሂዝቦላ አባል ማጅላል ሰልም በምትባል መንደር በመኪናቸው ላይ ጥቃት በመፈጸሙ ሊገደሉ ችለዋል
ከፍተኛ የሂዝቦላ ኮማንደር በእስራኤል የአየር ጥቃት መገደሉ ገለጸ።
እስራኤል በትናንትናው እለት በደቡብ ሊባኖስ በፈጸመችው የአየር ጥቃት በሂዝቦላው የሬድዋን ፎርስ ውስጥ የነበረው ከፍተኛ አዛዥ መግደሏን ሮይተርስ ዘግቧል።
ሮይተርስ የጸጥታ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው ግድያው በሬድዋን ፎርስ ውስጥ ያለ ቡድንን ምክትል አዛዥነት በሚመራው ዊሳም አል ታዊል ነው።
ዘገባው እንደጠቀሰው አል ታዊል እና ሌላ የሂዝቦላ አባል ማጅላል ሰልም በምትባል መንደር በመኪናቸው ላይ ጥቃት በመፈጸሙ ሊገደሉ ችለዋል።
"ይህ ዘግናኝ የሆነ ጥቃት ነው። ነገሮች ይቀጣጠላሉ" ሲሉ ሮይተርስ ያናገራቸው የጸጥታ ምንጮች ተናግረዋል።
ሀማስ በደቡብ እስራኤል ጥቃት ከሰነዘረበት ከባለፈው አመት ጥቅምት ወዲህ በእስራኤል የአየር ድብደባ 130 የሂዝቦላ አባላት ተገድለዋል።
ሌሎች 19 የሚሆኑ የቡድኑ አባላት ደግሞ በሶሪያ ተገድለዋል።
የሂዝቦላህ ዋና ጸኃፊ ሰይድ ሀሰን ነስረላህ እስራኤል በሊባኖስ ላይ ጠቅላላ ጦርነት እንዳትከፍት ባለፈው ሳምንት አስጠንቅቀዋል።