ሄዝቦላ ባወጣው መግለጫ በቤሩት የደረሰው የመሪ ግድያ በሌባኖስ ላይ የተቃጣ አደገኛ ጥቃት መሆኑን ገልጿል
ሄዝቦላ በእስራኤል ላይ የአጸፋ እርምጃ እወስዳለሁ ሲል ዛተ።
የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላ በትናንትናው እለት የሀማስ ምክትል መሪን በገደለችው እስራኤል ላይ የአጸፋ እርምጃ እወስዳለሁ ሲል ዝቷል።
የሀማስ የፖለቲካ ቢሮ ምክትል መሪ የነበረው ሳለህ አል አሮውሪ በሌባኖስ ዋና ከተማ ቤሩት ዳርቻ በምትገኝ መንደር ውስጥ ግድያ ተፈጽሞበታል።
ሄዝቦላ ባወጣው መግለጫ በቤሩት የደረሰው የመሪ ግድያ በሌባኖስ ላይ የተቃጣ አደገኛ ጥቃት መሆኑን ገልጿል።
ሄዝቦላ "በደቡብ ሊባኖስ ዳርቻ በምትገው መንደር መሃል ላይ የተፈጸመው የአል አሮሪ እና አብረውት የነበሩት ሰዎች ግድያ በሌበኖስ፣ በህዝቧ እና በደህንነቷ እና በሉአላዊነቷ ላይ የተቃጣ አደገኛ ጥቃት ነው፣ ይህ ወንጀል ምላሽ ሳይሰጠው ዝም ተብሎ አይታለፍም "ብሏል።
የመከላከል አቅማችን ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል ያለው ሄዝቦላ ተዋጊዎቹ በከፍተኛ ዝግጁነት ላይ መሆናቸውን ጠቅሷል።
እስራኤል በበኩሏ ሄዝቦለ ለሚሰነዝረው ማንኛውም ጥቃት ዝግጁ መሆኗን አስታውቃለች።
የእሴራኤል ጦር እንደገለጸው እስራኤል "ለሁሉም ቢሆኖች" ራሷን አዘጋጅታለች።
የአል አሮሪን ግድያ በቀጥታ ያላነሱት የጦሩ ቃል አቀባይ ዳንኤል ሀጋሪ በሰጡት መግለጫ ጦሩ "ለመከላከል እና ለማጥቃት በከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ ነው። ለሁሉም ቢሆኖች ዝግጁ ነን" ብለዋል።
ሀማስ የአል ቃሳም ብርጌድ ሁለት አባላት እና የሀማስ የፖለቲካ ቢሮ ምክትል ኃላፊን ጨምሮ ስድስት ሰዎች መገደላቸው በትናንትናው እለት ማስታወቁ ይታወሳል።
የባለፈው ጥቅምት ወር የእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ የሊባኖሱ ሄዝቦላህ ለሀማስ አጋርነት ለማሳየት በእስራኤል ላይ ተኩስ ከፍቷል።
ይህን ተከትሎ እስራኤለም፣ በሰሜን እስራኤል ተጨማሪ ግንባር ከፍታለች።