የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ሰርጌ ላቭሮቭ የፊታችን ማክሰኞ አዲስ አበባ ይገባሉ
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ሰርጌ ላቭሮቭ በአፍሪካ የሚያደርጉትን ጉብኝት በዛሬው እለት ጀምረዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ሰርጌ ላቭሮቭ በአራት የአፍሪካ ሀገራት የሚያደርጉትን ጉብኝት በግብጽ ካይሮ መጀመራቸውን ሲ.ጂቲ.ኤን ዘግቧል።
ሰርጌ ላቭሮቭ በግብጽ ቆይታቸው ከግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲሰ እና ከአረብ ሊግ ተወካዮች ጋር እንደሚወያዩም ተነግሯል።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከግብጽ ጉብኝታቸው ቀጥለው ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉብኝትም የፊታችን ማክሰኞ ይጀምራሉ።
በአዲስ አበባ የሩሲያ ኤምባሲ ለአል ዐይን አማርኛ እንዳስታወቀው የውጭ ጉጋይ ሚኒስትሩ የሁለት ቀናት ቆይታ ይኖራቸዋል።
የኤምባሲው ፕሬስ አታቼ ማሪያ ቸርኑኪና ለአል ዐይን እንዳሉት ዲፕሎማቱ በአዲስ አበባ ቆይታቸው ከአፍሪካ ህብረት ተወካዮች፣ ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት እና ከተለያዩ ሀገራት የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ጋር ይወያያሉ ተብሏል።
ላቭሮቭ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡም ፕሬስ አታቼ ማሪያ ቸርኑኪና አስታውቀዋል።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከኢትዮጵያ በመቀጠልም በኡጋንዳ እና በኮንጎ ሪፐብሊክ ጉብኝት እንደሚያደርጉም በአዲስ አበባ የሩሲያ ኤምባሲ አክሎ አስታውቋል።