ሰርጌይ ላቭሮቭ አሜሪካ በሩሲያ- አፍሪካ ግንኙነት ያላትን ምክንያታዊ ያልሆነ ስጋት ተቹ
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በ4 የአፍሪካ ሀገራት የሚየደርጉትን ጉብኘት በግብጽ ጀምረዋል
ፕሬዝዳንት ሲሲ “የሩሲያ -ዩክሬን ጦርነት በንግግርና በዲፕሎማሲ ሊፈታ የሚገባ ቀውስ ነው” ብለዋል
የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ፡ አሜሪካ በሩሲያ- አፍሪካ ግንኙነት ያለት ምክንያታዊ ያልሆነ ስጋት መተቸታቸወ ተገለፀ።
በአራት የአፍሪካ ሀገራት ጉብኝት ለማድረግ ወደ አፍሪካ ያቀኑት የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ሰርጌ ላቭሮቭ የመጀመሪያ ጉብኝታቸው በግብጽ ካይሮ አድርገዋል።
ሰርጌ ላቭሮቭ ከግብጽ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አልሲሲ ጋር በካይሮ ኤል-ኢቲሃዲያ ፕሬዝዳንታዊ ቤተ መንግስት በነበራቸው ቆይታ በዩክሬን እየተካሄደ ስላለው ግጭትና በአፍሪካ አህጉር ላይ ስላለው የእህል ቀውስ መወያየታቸውንም አር.ቲ ዘግቧል።
በውይይቱ ላቭሮቭ በዩክሬን ስላለው ቀውስ ወቅታዊ ሁኔታዎችን እና ጉዳዩን ለመቆጣጠር በሩሲያ በኩል በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተደረጉ ስላሉ ጥረቶች ለግብጽ ፕሬዝዳንት ገለፃ አድርገዋል።
ፕሬዝዳንት ሲሲ በበኩላቸው፤ የሩሲያ -ዩክሬን ጦርነት በንግግርና በዲፕሎማሲ ሊፈታ የሚገባ ቀውስ እንደሆነ ለሰርጌ ላቭሮቭ ገልጸውላቸዋል።
ቀውሱን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ግብጽ አስፈላጊውን ጥረት ለማድረግ ዝግጁ መሆኗም ጭምር ተናግረዋል ፕሬዝዳንቱ፡፡
በሌላ በኩል የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ፡ አሜሪካ በሩሲያ- አፍሪካ ግንኙነት ያላት ምክንያታዊ ያልሆነ ስጋት ተችተዋል፡፡
ከሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ጋር በተያያዘ የአፍሪካ ሀገራት ያሳዩት አቋም አሜሪካን ጨምሮ ምዕራባውያንን እንዳላስደሰተ እሙን ነው።
ይህን ተከትሎ አፍሪካውያን በጦርነቱ ያላቸውን አቋም ግልጽ እንዲያደርጉ ስትወተውት ለቆየችው አሜሪካ የሩሲያ-አፍሪካ ግንኙነት በቀላሉ ሊቃጥላት እንደማይችል በርካቶች ያነሳሉ።
የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት በተለይም አፍሪካ ላይ ከባድ የእህል አቅርቦት ከመፍጠሩ ጋር ተያይዞ አፍሪካ ህብረት ወቅቱ ሊቀ መንበር ማኪ ሳል በቅረቡ ወደ ሩሲያ አቅንተው ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር መወያየታቸው የሚታወስ ነው።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከግብጽ ጉብኝታቸው ቀጥለው ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉብኝትም የፊታችን ማክሰኞ የሚጀምሩ ይሆናል።
በአዲስ አበባ የሩሲያ ኤምባሲ ለአል ዐይን አማርኛ እንዳስታወቀው የውጭ ጉጋይ ሚኒስትሩ የሁለት ቀናት ቆይታ ይኖራቸዋል።
የኤምባሲው ፕሬስ አታቼ ማሪያ ቸርኑኪና ለአል ዐይን እንዳሉት ዲፕሎማቱ በአዲስ አበባ ቆይታቸው ከአፍሪካ ህብረት ተወካዮች፣ ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት እና ከተለያዩ ሀገራት የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ጋር ይወያያሉ ተብሏል።