ስለ ሸንገን ቪዛ ማወቅ ያሉብን አዳዲስ ውሳኔዎች ምን ምን ናቸው?
ሮማንያ እና ቡልጋሪያ የሸንገን ቪዛ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተወስኗል

ከጥር ጀምሮ አዳዲስ ሀገራት የሸንገን ቪዛ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ገልጿል
ስለ ሸንገን ቪዛ ማወቅ ያሉብን አዳዲስ ውሳኔዎች ምን ምን ናቸው?
የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን በፈረንጆቹ 1995 በአንድ ነጠላ ቪዛ ብዙ ሀገራትን መጎብኝት የሚያስችል ቪዛ ፕሮግራም ይፋ አድርጓል።
የሸንገን ስምምነት የሚባለው ይህ አዲስ ስርዓት ሀገራት ሸንገን ቪዛ በመስጠት የስምምነቱ ፈራሚ ሀገራት ዜጎች ያለ ፓስፖርት በበርካታ የአውሮፓ ሀገራት እንዲዘዋወሩ ይፈቅዳል።
ከዚህ በተጨማሪም የሸንገን ስምምነትን የፈረሙ ሀገራት ለጎብኚዎች የሚሰጡትን ቪዛ ተጠቅመው በብዙ የአውሮፓ ሀገራት በነጻ እንዲዘዋወሩ ይፈቅዳሉ።
ይሁንና የምስራቅ አውሮፓ ሀገራት የአውሮፓ ህብረት አባል ቢሆኑም የሸንገን ቪዛ ተጠቃሚ እንዳይሆኑ እገዳ ጥለዋል።
ለአብነትም የሮማንያ እና ቡልጋሪያ ዜጎች እንደ ጀርመን ፣ ፈረንሳይ፣ ሆላንድ እና ሌሎችም ሀገራት በሸንገን ቪዛ አማካኝነት እንዳይጓዙ እገዳ ተጥሎባቸው ነበር።
ሀገራቱ ቀስ በቀስ በሁለቱ ሀገራት ላይ የነበራቸውን ተቃውሞ በማቆማቸው ምክንያት ከጥር 1 ቀን 2025 ጀምሮ የሸንገን ቪዛ እንዲጠቀሙ ተፈቅዶላቸዋል።
የሮማንያ እና ቡልጋሪያ ዜጎች ወይም በሁለቱ ሀገራት ለመቆየት ቪዛ ያላቸው ጎብኚዎች በሸንገን ቪዛ አማካኝነት 25 የአውሮፓ ሀገራትን እንዲጎበኙ ተፈቅዶላቸዋል።
እንደ ዩሮ ኒውስ ዘገባ ከሆነ እስካሁን ከኦስትሪያ በስተቀር ሁሉም የሸንገን ስምምነት ፈራሚ ሀገራት የሮማንያ እና ቡልጋሪያ ዜጎች በነጻ እንዲጎበኟቸው ፈቅደዋል።
ከሁለት ዓመት በፊት ሌላኛዋ የምስራቅ አውሮፓ ሀገር ክሮሽያ የሸንገን ቪዛን እንድትጠቀም ተፈቅዶላት ነበር።
አንድ የሸንገን ቪዛ ያለው ሰው ከ400 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላቸው 25 የአውሮፓ ሀገራትን እንዲጎበኝ ይፈቀዳል።
በዚህ የሸንገን ስምምነት አማካኝነት በየዕለቱ 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሰዎች የአውሮፓ ሀገራት ድንበሮችን ያቋርጣሉ።
በአጠቃላይ በሸንገን ቪዛ አማካኝነት 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ጉዞዎች በአውሮፓ ሀገራት መካከል ይካሄዳልም ተብሏል።
በአውሮፓ አህጉር ስር 44 ሀገራት ያሉ ሲሆን 25ቱ የአውሮፓ ህብረት አባል ሆነዋል።