የአረብ ኢምሬትሱ ሼህ ከሊፋ ቢን ዛይድ አልናህያን ሲታወሱ
የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝንት ሼህ ከሊፋ ቢን ዛንድ አልናህያን ካረፉ ዛሬ አንድ አመት ሆኗቸዋል
ሼህ ከሊፋ ቢን ዛይድ አልናሃያን ህይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ለ18 አመታት ሀገሪቱን መርተዋል
የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝንት ሼህ ከሊፋ ቢን ዛንድ አልነህያን ካረፉ ዛሬ አንድ አመት ሆናቸዋል።
ሼህ ከሊፋ ቢን ዛይድ አልነህያን በ74 አመታቸው ነበር ህይወታቸው ያለፈው።
በፈረንጆቹ 2004 ስልጣን የያዙት ሼህ ከሊፋ ቢን ዛይድ አልነሃያን ህይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ለ18 አመታት ሀገሪቱን መርተዋል።
ሼህ ከሊፋ ቢን ዛይድ አልነሃያን ማረፋቸውን ተከትሎ ልጃቸው ሼህ መሀመድ ቢን ዛይድ አልነህያን በእሳቸው ቦታ ተተክተው ስልጣን ይዘዋል።
ሼህ መሀመድ ቢን ዛይድ አልነሃያን በፈረንጆቹ ግንቦት 14 ስልጣን ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ ሼህ ከሊፋ ቢንጰዛይድን ያላመሰገኑበት ወይም ያላወሱበት አጋጣሚ የለም።
ሼህ መሃመድ ቢን ዛይድ አልነሃያን የሼህ ከሊፋ ቢን ዛይድ አልነሃያን ውጥን ስራዎችን ከግብ ለማድረስ ቃል ገብተዋል።
ይህንን ሼህ መሃመድ ቢን ዛይድ አልነሃያን የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝደንት ሆነው ሲሾሙ ባደረጉት የመጀመሪያ ንግግር ላይ አንጸባርቀውታል።
ሼህ መሃመድ ቢን ዛይድ አልነሃያን በጠቅላይ ምክርቤቱ በአብላጫ ድምጽ ተመርጠው ነው የፌደሬሽኑ ኘሬዝደንት መሆን የቻሉት።
ሼህ መሀመድ ቢን ዛይድ አልነሃያን ያደረጉትን የስልጣን ሽግግር መላው አለም የተከታተለው ክስተት ሆኖ ነበር።