ሀገሪቱ በሱዳን የሚፈለገውን የፖለቲካ መረጋጋትና ደህንነትን ለማስፈን የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስባለች
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ዜጎቿን እና የበርካታ ሀገራት ዜጎቿን ከሱዳን ሪፐብሊክ አስወጥታለች።
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በፖርት ሱዳን ከተማ ዜጎቿን ለማስወጣት ባደረገችው እንቅስቃሴ የ19 ሀገራት ዜጎችም አብራ ማስወጣቷን ተናግራለች።
ዜጎቹ ወደ ሀገራቸው ከመዛወራቸው በፊት በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ይስተናገዳሉም ተብሏል።
ሀገሪቱ ለሰብዓዊ እርዳታ በገባችው ቃል መሰረት ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጠናከር ዜጎቿን እና የበርካታ ሀገራት ዜጎችን ከሱዳን ማስወጣቷን የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚንስቴር አስታውቋል።
እርምጃው ለሲቪሎች ጥበቃ ለመስጠትና በችግር ጊዜ ለሀገሮች እርዳታን ለማዳረስ ሲባል መወሰዱ ተገልጿል።
ሚንስቴሩ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከአጋሮቿ እና ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር በመሆን የሱዳንን ህዝብ ጥቅም ለማስከበር ቁርጠኝነትን አሳይተዋል ብሏል።
ከዚህ ባለፈም በሱዳን የሚፈለገውን የፖለቲካ መረጋጋትና ደህንነትን ለማስፈን የተኩስ አቁምን ለማስፈን እንዲሁም ወደ ፖለቲካዊ ውይይት ለመመለስ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ሚንስቴሩ አሳስቧል።