አረብ ኤምሬትስ በሰብዓዊ መብት አያያዝ ዙሪያ ላስመዘገበችው ለውጥ ተወደሰች
ዓለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ጥምረት ለተመዘገበው ስኬት የሀገሪቱን ህዝብና መንግስት አወድሷል
አረብ ኤምሬትስ በሰብአዊ መብቶች፣ የአየር ንብረት ፍትህን በማሳካትና በዘላቂ ልማት ሞዴል መሆኗን ጥምረቱ አስታውቋል
ዓለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ጥምረት አረብ ኤምሬትስ በሰብዓዊ መብት አያያዝ ዙሪያ ላስመዘገበችው ለውጥ አመሰገነ።
ጥምረቱ አረብ ኤሚሬትስ ዜጎች እና መሪዎቻቸው በሰብአዊ መብቶች እና ነፃነቶች መስክ፣ የአየር ንብረት ፍትህን በማሳካት እንዲሁም በዘላቂ ልማት ውስጥ አበረታች ሞዴል በማቅረብ ያሳዩትን ታላቅ ስኬት አወድሰዋል።
ከ53 ሀገራት የተውጣጡ ዓለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በውስጡ የያዘው ጥምረቱ አረብ ኢሚሬትስ በመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና በሰብዓው መብት አያያዝ ለውጥ ካመጡ ሀገራት ውስጥ በቀዳሚነት አስቀምጧታል።
ጥምረቱ በሰብአዊ መብት አያያዝ ላይ ያተኮረ ሲሆን ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ስኬቶችን ላስመዘገቡ ሀገራት ሁሉን አቀፍ ወቅታዊ የግምገማ ዘዴ በመጠቀም ውጤት የሚሰጥ ነው።
ጥምረቱ የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ አመራር ለሰብአዊ መብት መርሆዎችና እሴቶች ያላቸውን ቁርጠኝነት በማጤን ሪፖርቱን ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያቀረበ ሲሆን፤ የሀገሪቱ መንግስት መንግስት የሰብአዊ መብት መከበርን በማሳደግ ረገድ ያደረጋቸውን ጥረቶች እና ስኬቶችን አቅርቧል።
ጥምረቱ ሪፖርቱን ያቀረበው በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሰብአዊ መብት ልማትን ለመፈተሽ ባደረገው ዓለም አቀፍ ዝግጅት ላይ ነው።