ዩኤኢ ከኮሮና ቀውስ ወጥታ ወደ ቀድሞ መደበኛ እንቅስቃሴ ተመልሳለች- ሼህ ሞሃመድ ቢን ዛይድ
በዩኤኢ ያለው የጤና ጥበቃ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝም አስታውቀዋል
ኮሮና ቫይረስ ብዙ ዋጋ ቢያስከፍለንም መልካም ተሞክሮ ተምረንበት ተሻግረነዋል ብለዋል ሼህ ሞሃመድ ቢን ዛይድ
የየተባበሩት አረብ ኤምሬቶች (ዩኤኢ) ከኮሮና ቀውስ ወጥታ ወደ ቀድሞ መደበኛ እንቅስቃሴ መመለሷን አስታወቀች።
የአቡዳቢ አልጋወራሽና የየተባበሩት አረብ ኤምሬቶች (ዩኤኢ)ምክትል የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሼህ ሞሃመድ ቢን ዛይድ አልነሃያን ዛሬው እለት በሀገሪቱ ባለው የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።
ሼህ ሞሃመድ ቢን ዛይድ አልነሃያን በመግለጫቸው “መልካም ነገር እንዳለ ላበስራችሁ እወዳለሁ፤ የጤና ጥበቃ ሁኔታ በኤምሬት በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል ሲሉ ተናረዋል።
“ለሁለችሁም ማረጋገጥ የምችለው ህይወታችን ወደ ነበረበት ተፈጥሯዊ ሁኔታ እንደሚመለስ ነው” ሲሉም በሀገሪቱ ያለው እንቅስቃሴ ቀድሞ መደበኛው መመለሱን አስታውቀዋል።
ሆኖም ግን አንድ አንድ ባህላዊ ልምዶቻችን በጥቂት ሊቀየሩ ይችሉ ይሆናል ያሉት ሼህ ሞሃመድ ቢን ዛይድ የሚስተካከሉ ወይም የሚሻሻሉ ሊኖሩ እንደሚችሉም ጠቅሰዋል።
ከኮሮና ጋር በተያያዘ ሊቀየሩ ችላሉ ካሏቸው ውስጥም ቤተሰባዊ መጠያየቀቅ፣ የስራ ሁኔታ እና የልጆች ትምህርት፣ የግል የህይወት እንቅሳቃሴዎች” ይገኙበታል።
“ከዚህ አስቸጋሪ ጭንቅ ስላወጣን አላህን በሁሉ ነገር ሁኔታ እናመሰግናለን” ያሉት ሼህ ሞሃመድ ቢን ዛይድ አልነሃያን “ኮሮና ቫይረስ ብዙ ዋጋ ቢያስከፍለንም መልካም ተሞክሮ ተምረንበት ተሻግረነዋል” ብለዋል።
“ስለ ተገናኘንና ስላየኋችሁ ፈጣሪዬን አመስግነዋለሁ” ሲሉም ተናግረዋል።
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ስርጭቱን ለመቆጣጠተር ዜጎች ከቤት እንዳይወጡ ማድረግን ጨምሮ በሀገሪቱ የሚገኙ ሁሉም የገበያ ማእከላት እና ሞሎች የአሳ፣ የስጋና የአትክልት ገበያዎችን ዝስከመዝጋት የሚደርሱ ውሳኔዎችን አሳልፋ ነበር።