ባንኩ ምንም አይነት ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የማይጠቀም ሲሆን ጠቅላላ ሀብቱ 3 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው
በሁለት ሰራተኞች የሚንቀሳቀሰው አንድ ክፍለ ዘመን ያስቆጠረው የአሜሪካ ባንክ።
የአሜሪካዎቹ ጂፒ ሞርጋን፣ ሞርጋን ስታንሌይ፣ ሲቲግሩፕ፣ ዌልስ ፋርጎ፣ ባንክ ኦፍ አሜቲካ በዓለም ላይ ተጽዕኖ ፈጣሪ ባንኮች ናቸው።
እነዚህ ባንኮች የዓለም ባንክ ቴክኖሎጂን በመምራት የመታወቃቸውን ያህል ከነዚህ ባንኮች በፊት ከተቋቋመ ሌላ ባንክ እንዳለ ያውቃሉ?
ዋና መቀመጫውን በአሜሪካዋ ኢንዲያና ያደረገው ኬንትላንድ ፌደራል ቁጠባ እና ብድር ባንክ የተሰኘው ተቋም በፈረንጆቹ 1920 ላይ ነበር።
ይህ ባንክ እንደሌሎች ባንኮች እየዘመነ እና ትርፉ እያደገ ከመሄድ ይልቅ ባለበት ብቻ ቀርቷል ሲል ብሉምበርግ ዘግቧል።
- ሆነ ብለው እስር ቤት ለመግባት ከባንክ 1 ዶላር የዘረፉት አሜሪካዊው አዛውንት
- የብሪታኒያ ብሄራዊ ባንክ የሀገሪቱን ዜጎች “እየደኸያችሁ መሆኑን ልትረዱ ይገባል” አለ
የባንኩ አጠቃላይ ሀብት ሶስት ሚሊዮን ዶላር ብቻ ሲሆን ኤቲኤምን ጨምሮ ሌሎች ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችንም እየሰጠ አይደለም ተብሏል።
ባንኩ ከ100 ዓመት በፊት አገልግሎት ሲጀምር ባለበት ነው የተባለ ሲሆን ለተወሰኑ ሰዓታት ብቻ ለባንኩ ቋሚ ደንበኞች አገልግሎት የሚሰጡ ጊዜያዊ ሰራተኞች አሉት።
ይህ ተቋም አገልግሎቱን እየሰጠ ያለው እጅግ ኋላ ቀር በሆነ በእጅ በሚንቀሳቀስ ማሽን ሲሆን አንድ ቅርንጫፍ ብቻ እንዳለውም ተገልጿል።
የአሜሪካ መንግሥት በተደጋጋሚ ይህ ባንክ ከሌሎች ባንኮች ጋር እንዲዋሀድ እና የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ ማስጠንቀቂያ ቢሰጥም አሁንም ህልውናውን አስቀጥሏል ተብሏል።
አሁን ላይ የአሜሪካ ግዙፍ ባንኮች ሳይቀር ፈተና የገጠማቸው ሲሆን ይህ እድሜ ጠገብ ባንክ የመክሰም አደጋ እንደተጋረጠበት የባንኩ ስራ አስኪያጅ ተናግረዋል ።
የ54 ዓመቱ ስራ አስኪያጅ እንዳሉት ከሆነ ባንካቸውን የመምራት ፍላጎት ያለው ሰው እንደሌለ እና እሳቸው ስራ ቢያቆሙ ባንኩም አብሮ እንደሚከስም ተናግረዋል።
የአሜሪካ ባንክ ተቆጣጣሪ ባለስልጣናት ይህ ባንክ ከመክሰሙ በፊት መላ እንዲፈልግ አሁንም በማሳሰብ ላይ ናቸው ተብሏል።