ሆነ ብለው እስር ቤት ለመግባት ከባንክ 1 ዶላር የዘረፉት አሜሪካዊው አዛውንት
በፈረንጆቹ 2011 እና 2012 በሰሜን ካሮላይና እና ካሊፎርኒያ ተመሳሳይ የባንክ ዘረፋዎች ተፈጽመው ነበር
ድርጊቱን የፈጸሙት ግለሰብ የባንክ ሰራተኞች ለፖሊስ ደውለው እንዲያስዟቸው ጠይቀዋልም ነው የተባለው
በሀገረ አሜሪካ የተፈጸመው የባንክ ዘረፋ ድርጊት በበርካቶች ዘንዳ ግርምት የፈጠረ ሆኗል፡፡
- የአሜሪካ ኮንግረስ አባል በጠራራ ጸሃይ መኪናቸውን መዘረፋቸው እያነጋገረ ነው
- ሱዳን በሰሜን ዳርፉር ግዛት የአለምአቀፍ ድርጅቶችን ዘረፋ ለመቆጣጠር የሰዓት እላፊ አወጀች
የ65 አመቱ ዶናልድ ሳንታክሮስ ዩታ ግዛት ከሚገኘው ባንክ 1 ዶላር ዘርፏል በሚል ተይዘው በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ነው ሮይተርስ የዘገበው፡፡
አዛውንቱ ድርጊቱን የፈጸሙት ሆነ ብለው ወደ ፌዴራል እስር ቤት ለመሄድ በማሰብ መሆኑም ነው የገዛቱ ባለስልጣናት የገለጹት፡፡
ዶናልድ ሳንታክሮስ ዘረፋ በፈጸሙበት በሶልት ሌክ ሲቲ ወደሚገኝ ዌልስ ፋርጎ አካባቢ እንደገቡ ለሰራተኞቹ “እባካችሁ ይህን በማድረጌ ይቅርታ አድርጉልኝ ነገር ግን ይህ ዘረፋ ነው፤ እባካቸውሁ 1 ዶላር ስጡኝ፤ አመሰግናለሁ" የሚል ይዘት ያለው ብጣሽ ወረቀት ለባንኩ ሰራተኞች መስጠታቸውንም ባለስልጣናቱ ተናግረዋል፡፡
ሳንታክሮስ በዚህ አላበቁም የባንክ ሰራተኞቹ ለፖሊስ ደውለው እንዲያስዟቸው ጠይቀዋል ነው የተባለው፡፡
ዶናልድ ሳንታክሮስ የባንክ ሰራተኞቹ በጥቆማ እንዲያስዟቻ ቢጠይቁም፤ በህግ አስከባሪ ፖለሲች በኩል የነበረው ምላሽ አጅግ የዘገየ እንደነበር ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡
“የባንኩ ሰራተኞች እድለኞች ናቸው፤ ሽጉጥ ቢኖረኝስ?” ሲሉም ነው ፖሊሶቹን የወቀሱት፡፡
የአሜሪካው ኤንቢሲ እንደዘገበው የወንጀል ድርጊቱ በሶልት ሌክ ካውንቲ ከተፈጸሙ ከባድ ዝርፊያዎች አንዱ ሆኖ መመዝገቡን ዘግቧል፡፡
ሳንታክሮስ በሰጡት ቃል ባንኩን የዘረፍኩት “ተይዜ ወደ ፌደራል እስር ቤት መሄድ ስለፈለኩ ነው” ብለዋል፡፡
በቀጣይ በሌሎች ባንኮች ላይ መሰል ዘረፋዎች በመፈጸም የመታሰር እቅድ እንዳላቸውም ጭምር ገልጸዋል፡፡
ሳንታክሮስ ለምን ራሳቸውን በእስር ቤት ለመክተት ፈለጉ ለሚለው ግን በግልጽ የታወቀ ምክንያት የለም፡፡
እንደፈረንጆቹ በ2011 እና 2012 በሰሜን ካሮላይና እና ካሊፎርኒያ ተመሳሳይ የባንክ ዘረፋ ድርጊቶች ተፈጽመው እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
በሰሜን ካሮላይና በነበረው ክስተት ወንጀለኛው ድርጊቱን የፈጸመው በእስር ቤት ውስጥ የጤና እንክብካቤ ለማግኘት ነበር፡፡
የካሊፎርኒያው ተጠርጣሪም እንዲሁ መጠለያ እና መድሃኒት ለማግኘት እንደነበር ይታወሳል፡፡