የብሪታኒያ ብሄራዊ ባንክ የሀገሪቱን ዜጎች “እየደኸያችሁ መሆኑን ልትረዱ ይገባል” አለ
በብሪታንያ ሰራተኞች የደመወዝ ማስተካከያ እንዲደረግ በመጠየቅ ላይ ናቸው
በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ምክንያት በአውሮፓ የዋጋ ግሽበት ማጋጠሙ ይታወሳል
ብሪታንያዊያን እየደኸዩ መሆኑን እንዲረዱ የሀገሪቱ ብሄራዊ ባንክ አሳሰበ።
ከ15 ወራት በፊት የተጀመረው የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት የዓለምን ምግብ እና ነዳጅ ዋጋ ያናረ ሲሆን በአውሮፓ ደግሞ በታሪክ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት አስከትሏል።
ይህን የዋጋ ግሽበት ተከትሎም የተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት መንግስቶቻቸው የኢኮኖሚ ማሻሻያ እንዲያደርጉላቸው በተለያየ መንገድ እየጠየቁ ይገኛሉ።
በብሪታንያም ተመሳሳይ ጥያቄዎች ስራ ማቆም አድማን ጨምሮ በብዙ መንገዶች የኢኮኖሚ ማሻሻያ እንዲደረግ የጠየቁ ሲሆን የደመወዝ ይጨመርልን ዋነኛው ነው።
የእንግሊዝ ብሔራዊ ባንክ ከፍተኛ ኢኮኖሚስ የሆኑት ሁው ፒል በአሜሪካ ኮሎምቢያ ዩንቨርሲቲ በተዘጋጀ ፕሮግራም ላይ እንዳሉት የብሪታንያ ዜጎች እየደኸዩ መሆኑን ሊቀበሉ ይገባል ብለዋል።
የሀገሪቱ ዜጎች እየደኸዩ መሆኑን ካልተቀበሉ ፍላጎታቸው እየጨመረ እና የዋጋ ግሽበቱም መጨመሩ አይቀርም ሲሉም ኢኮኖሚስቱ ተናግረዋል።
የኑሮ ውድነቱ መጨመሩን ተከትሎ የደመወዝ ጭማሪ መጠየቅ የዋጋ ንረቱን አያቆመውም ያሉት ባለሙያው ከዛ ይልቅ ፍላጎትን መቀነስ እና ሌሎች እርምጃዎችን መከተል እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል።
የባንኩ ባለሙያን አስተያየት ተከትሎ ብርካታ ብሪታንያዊያን በብስጭት በተለያየ መንገድ ምላሽ በመስጠት ላይ ናቸው ተብሏል።
በብሪታንያ ያዋጋ ግሽበቱ በመጋቢት ወር ከ10 በመቶ በላይ ሲሆን ይህም በብሪታንያ ታሪክ ከፍተኛው እንደሆነ ተገልጿል።